ተማሪዎች በፈጠራ ስራ ያላቸው አቅም በማሳደግና የሚሰሩዋቸው የፈጠራ ውጤቶች ወደ ቴክኖሎጂ በማሸጋገር ዘርፉ እንዲነቃቃ የበለጠ መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ አስታወቀ።


ተማሪዎች በፈጠራ ስራ ያላቸው አቅም በማሳደግና የሚሰሩዋቸው የፈጠራ ውጤቶች ወደ ቴክኖሎጂ በማሸጋገር ዘርፉ እንዲነቃቃ የበለጠ መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን የተማሪዎች፣ የመምህራን እና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ሰልጣኞች የፈጠራ ስራ ኤግዚቢሽን ፕሮግራም በአገና ከተማ ዛሬ በይፋ ተጀመረ።

የእዣ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ከወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት በጋራ በመሆን የፈጠራ ስራዎች ኢግዚብሽን ማስጀመሪያ መድረክ በአገና ከተማ አድርገዋል።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ አለም ያደገችውም የምታደገውም በፈጠራ ስራ ሲሆን የፈጠራ ሰዎች ደግሞ የሚወጡት ከትምህርት ቤት ነው ብለዋል።

በወረዳው በርካታ የፈጠራ ሰዎች ያሉ ሲሆን ወረዳውም ለሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ትኩረት በመስጠቱ ግንባር ቀደም ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመላክተዋል።

የሚሰሩ የፈጠራ ስራዎችና ባለሙያዎች የት እንደደረሱ መከታተል፣መደገፍና ማብቃት ይገባል ያሉት አቶ ደምስ በአምና ደረጃ እውቅና አግኝተው ያለፉ የፈጠራ ባለቤቶች በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ እንዲደገፉ ተደርጓል ነው ያሉት።

አቶ ደምስ አክለውም የፈጠራ ሰዎች ሀሳባቸው ወደ ተግባር በመለወጥ የህብረተሰቡ ችግር መቅረፍ እንደሚገባቸው እና ኢንተርፕራይዞች ደግሞ የሚመጣላቸው ፈጠራዎች ወደ ተግባር መቀየር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ፕሮግራሙ ከዛሬ ጀምሮ በዞኑ ባሉ መዋቅሮች እንደሚካሄድ ገልጸው ተማሪዎች በፈጠራ ስራ ያላቸው አቅም በማሳደግና የሚሰሩዋቸው የፈጠራ ውጤቶች ወደ ቴክኖሎጂ በማሸጋገር ዘርፉ እንዲነቃቃ መስራት እንደሚገባ አስታውቋል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንዳሉት እንዳሉት የፈጠራ ዘርፉ ተማሪዎች ያላቸው እውቀት፣አቅም እና ልምዳቸው የሚያወጡበት ነው ያሉ ሲሆን እነዚህ ናሙናዎች ወደ ሀብት መቀየር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

አቶ ዘውዱ አክለውም የፈጠራ ባለሙያዎች የህብረተሰቡ መሰረታዊ ችግር ምን እንደሆነ በጥልቀት በማጤን ችግር ፈቺ ስራዎች ማቅረብ እና እራሳቸውም ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚችሉ መክረዋል።

የጉራጌ ማህበረሰብ በራሱ በፈጠራ ስራ የሚታወቅ ለዘርፉ ልምድ ያለው ህዝብ ነው።በመሆኑም ወረዳውም በተማሪዎች የፈጠራ ስራ ትኩረት በመስጠት ለዞን፣ለክልል፣ለሀገር አልፎ ለአለም የሚጠቅሙ ተማሪዎች እንዲወጡ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

የእዣ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እረሂማ ሙክታጅ የፈጠራ ስራው ውጤታማ ለማድረግ በዘርፉ የሚገጥሙ የግብአት፣የበጀት ችግሮች መቅረፍ እንደሚገባና ኮሌጆች፣ክበባትና መምህራን የበኩላቸው መወጣት አለባቸው ያሉ ሲሆን እስካሁን ለ17 ትምህርት ቤቶች የማቴሪያልና ሌሎች መሰል ድጋፎች መደረጉ አስታውቀዋል።

የፈጠራ ባለቤቶች በሰሩዋቸው ስራዎች የአእምሮአዊ ንብረት እውቅና ለ5 የፈጠራ ስራዎች ፕሮፖዛላቸው በመገምገምና መሰፈርቶች በማሟላት ወደ ኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጥበቃ ጽ/ቤት መላኩ አስታውሰዋል።

ከኮሌጅ፣ከዞኑ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያና ከሚመለከታቸው ተቋማት ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ገልጸው መሰል አይነት መድረኮች ተማሪዎች የበለጠ በሙያቸው የበለጠ እንዲነቃቁ ያደርጋል።

በኢግዚብሽኑ የተሳተፉ መምህራንና ተማሪዎች እንዳሉት በአካባቢያችን የህብረተሰቡ ችግር የሆኑትን በመለየት የማህበረሰቡ ጉልበት፣ጊዜና ገንዘብ ለመቆጠብ በርካታ የፈጠራ ስራዎች እንድንስራ መነሳሳሳት ፈጥሮብናል ሲሉ ገልጸዋል።

በዚህ ውድድር የኬሚካል መርጫ ማሽን፣ሰርኪውድ ቦርድ፣የመበየጃ ማሽን ክፍለ ጊዜ መቆጣጠርያ፣ አፓርትመንት፣እስቶቭ፣የትራፊክ መቆጣጠሪያ ማሽን፣ፔሬዲክ ቴብል፣ዉሃ ማፊያ፣የጉድጓድ ውሃ ማውጫ፣ሳምብል ሄሊኮብተር ኬሚካሎች እና ሌሎችም አቅርበዋል።

በዘርፉ የሚገጥሙ የግብአት እጥረቶች እንዲቀረፍላቸው የጠየቁት መምህራንና ተማሪዎቹ የህብረተሰቡ ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ የፈጠራ ስራዎች በመስራት በሁሉም ቦታ ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚሰሩ ተናግሯል።

በመጨረሻም በፈጠራ ስራ የተሻለ ስራ ላቀረቡ ተማሪዎች፣መምህራን፣ኢንተርፕራይዞች፣የትምህርት ተቋማት እና ድጋፍ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *