ተማሪዎች በመማሪያ ቁሳቁስ እጦት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሆነ የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

ጥቅምት 5/2015 ዓም

ተማሪዎች በመማሪያ ቁሳቁስ እጦት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሆነ የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያዉ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲና ከጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር በድጋፍ ያገኛቸዉን የትምህርት ቁሳቁሶችን ለወረዳዎችና ከተማ አስተዳድር ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ተደራሽ እያደረገ እንደሆነም ተጠቁሟል።

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የትምህርት ቤት መሻሻል ባለሙያ አቶ ለገሰ ጋዲሳ እንዳሉት በትምህርት ቁሳቁስ ማጣት ህጻናት ትምህርት እንዳያቋርጡና በተገቢዉ ትምህርታቸዉ እንዲማሩ በትኩረት እየተሰራ ነዉ።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና የጉራጌ ባህልና ልማት ማህበር በዞኑ በሚገኙ ለሁሉም ወረዳና ከተማ መስተዳድር አቅም ለሌላቸዉ ህጻናት የሚሆን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸዉም አብራርተዋል።።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ 3ሺህ ያህል ደብተር እና 1500 እስክሪብቶ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ይህም በገንዘብ ሲቲን ወደ 18 ሺህ ብር ይገመታል ያሉት አቶ ለገሰ የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ከ18 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አብራርተዋል።

በድጋፍ የተገኙ የትምህርት ቁሳቁሶች ወላጆች ለልጆቻቸዉ ደብተር ገዝተዉ ማስተማር ለማይችሉ ከየወረዳና ከተማ መስተዳድር ለተዉጣጡ ወገኖች ድጋፍ የሚደረግ ሲሆን ይህንንም በተገቢዉ ለማዳረስ ስም ዝርዝር ተወስዶ እየተሰራ እንደሆነም አመላክተዋል።

ተማሪዎች በመማሪያ ቁሳቁስ እጦት ትምህርት እንዳያቋርጡ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰሩ እንደሆነም ያብራሩት አቶ ለገሰ በዘንድሮ አመት በተለያዩ አካባቢዎች በባለሀብት ፣ በመንግስት ፣ በሌሎች ለጋሽ ድርጅቶችና በጎ ፍቃደኞች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍን ሲደረግ እንደነበረም አስታዉሰዉ ይህም በጎ ልምድ የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል።

የቀቤና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሪት ፋይዛ አለዊ እና የወልቂጤ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የትምህርት ቤቶች ማሻሻል ዳይሬክቶሮት ዳይርክተር ወይዘሮ ሰሚራ አብራር የትምህርት ቁሳቁሱ ርክክብ ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት መማር እየቻሉ የአቅም ችግር ያለባቸዉ ህጻናት ከትምህርት ገበታቸዉ እንዳይርቁ ተደረገላቸዉ ድጋፍ አጋዥ እንደሆነም አስታዉቀዋል።

ከክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ጀምሮ ወጣቶችን፣ የልማት ማህበራት ድርጅቶችና ባለሀብቶች በማስተባበር ለበርካታ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እንደተደረገላቸዉም አስታዉሰዉ ዛሬም ከዞኑ ትምህርት መምሪያ የተረከቡትን ደብተርና እስክሪፕቶ በተገቢዉ ተደራሽ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

በመጨረሻም የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸዉ ተማሪዎች ለተደረገላቸዉ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Tiwter https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *