ተመራቂ ተማሪዎች ስራ ጠባቂ ሳይሆኑ በተግባርና በንድፈ ሀሳብ ያገኙት እውቀትና ክህሎት ተጠቅመው በግልና በቡድን ተደራጅተዉ መስራት እንዳለባቸዉ የደቡብ ክልል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ገለጸ።

የሐዋሪያት ኮንስትራክሽንና ኢንዲስትሪያል ኮሌጅ ለሁለተኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸዉ 2 መቶ 27 ሰልጣኞችን አስመረቀ።

ከክልል ፣ ከዞንና ከወረዳዉ የተዉጣጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በኮሌጁ የተለያዩ ዝርያ ያለቸዉን ችግኞች ተክለዋል።

ኮሌጆች የሰለጠነ የሰው ሀይል በብዛትና በጥራት በማምረት ለኢንዱስተሪዎች በማስተላለፍና አዳዲስ ቴክኖሎጂ ለመፍጠር እያደረጉት ያለዉን በጎ ጅምር የሚበረታታ ነዉ።

የደቡብ ክልል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ታመነ ገብሬ እንደገለፁት የቴክኒክ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ለማፋጠን የዜጎች ቴክኖሎጂ የመጠቀም አቅም ለማሳደግ ያለው ሚና የጎላ ነው።

ተመራቂ ሰልጣኞች ስራ ጠባቂ ሳይሆኑ በተግባርና በንድፈ ሀሳብ ባገኙት እውቀትና ክህሎት ተጠቅመው በግል ሆነ በቡድን በመደራጀት ስራ በመስራት እራሳቸውን፣ ቤተሰባቸው እ ብሎም ሀገራቸውን ተጠቃሚ ማድረግ እንዳለባቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የሙህርና አክሊል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብስራት ገብሩ እንዳሉት ኮሌጁ የአካባቢዉ ማህበረሰብ ችግር የሚቀርፉ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂ በመፍጠር የድርሻዉን መወጣት ይኖርበታል።

ወረዳዉ በየአመቱ ለተቋሙ አቅም በፈቀደ መልኩ በቁሳቁስና በበጀት ድጋፍ የሚያደርግ እንደሆነም ተናግረዉ ቀጣይም በኮሌጁ እየተሰራ ያለዉን ስራ የበለጠ ዉጤታማ እንዲሆን ድጋፉን ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታዉቀዋል።

ተመራቂ ተማሪዎችም በቆይታቸዉ ያገኙትን ዕዉቀት ወደ ዉጤት በመለወጥ ስራ ፈጥረዉ በመስራት እራሳቸዉንና ማህበረሰቡን መገልገል እንዳለባቸዉም አሳስበዋል።

የሀዋሪያት ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲን አቶ ትዛዙ ፍቃዱ በምረቃዉ እንዳሉት በአይ ሲቲ ፣በአዉቶሞቲቭ ፣ በዉድወርክ፣ በኤሌክትሮ ፣ በሜታል ወርክና በኮንስትሬክሸን ቴክኖሎጂ ለሁለተኛ ዙር እስመረቀ ይገኛል።

ኮሌጁ ለህብረተሰቡ እየሰጠዉ ያለዉን አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሆነም አስረድተዉ በዛሬዉ ዕለት በስድስት የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸዉ 227 ሰልጣኞች ማስመረቃቸዉም ገልጸዋል ።

ከተመራቂዎች መካከል 123 በደረጃ አንድና ሁለት ፣104 በደረጃ ሶስትና አራት መሆናቸዉም አስታዉቀዋል።

የጉራጌ ዞን አስተዳዳር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ አካሉ ተመራቂ ተማሪዎች በሰለጠኑት ሙያ ራሳቸውንና ማህበረሰባቸውን መጥቀም አንዳለባቸው ገልጸው ኮሌጁ የሰለጠነና ብቁ ዜጋ ለማፍራት በሚያደርገው ጥረት የዞኑ አስተዳደር የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ራሄል ማሞ ፣በሰጡት አስተያየት በኮሌጁ ቆይታቸዉ ያገኙትን እዉቀት ተጠቅመዉ ስራ በመፍጠር ማህበረሰቡን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸዉም ተናግረዋል
በምረቃው ስነ ስርዓት የተሳተፊ የክልል የዞንና የወረዳው አመራሮና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሐዋሪያት ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ግቢ ውስጥ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል የሲል የዘገበው ዉጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *