ብቁና ተነሳሽነት ያለው ሥራ ፈጣሪ ዜጋን እንፈጠራለን በሚል መርህ የ2015 ዓም የሥልጠና ዘመን በይፋ መጀሩን በጉራጌ ዞን የቡታጀራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ገለፀ።

ጥቅምት 2/2015 ዓ.ም

ብቁና ተነሳሽነት ያለው ሥራ ፈጣሪ ዜጋን እንፈጠራለን በሚል መርህ የ2015 ዓም የሥልጠና ዘመን በይፋ መጀሩን በጉራጌ ዞን የቡታጀራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ገለፀ።

በዞኑ በሚገኙ ሁሉም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በተመሳሳይ ቀን የዓመቱን ስልጠና መጀመራቸው ተገለፀ ።
የኮሌጁ ግቢ ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ ለማድረግ በዕለቱም የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል።

የቡታጀራ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ አብዱልዋሒድ መሀመድ እንዳሉት ሁሉም ኮሌጆች ጥቅምት 1/2015 ዓ.ም ሥልጠና እንዲጀመር በተቀመጠው መሠረት ከመስከረም 23 እስከ 27/2015ዓ.ም የመደበኛ ተማሪ ምዝገባ ማጠናቀቃቸዉም አስታዉሰዉ ጥቅምት 1/2015 መደበኛ ትምህርት ማስጀመራቸውን ገልፀዋል።

በኮሌጁ ብቁና በሙያዉ የሚተማመን ዜጋ በብዛትና በጥራት ለማምረት የአይ ሲቲ ኢንፍራስትራክቸር ዝርጋታ 100 ፐርሰንት በማጠናቀቅ ሁሉም የመማሪያ ማዕከላት ኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽ የማድረግ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

ጥራት ያለዉ ስልጠና ለመስጠት ኮሌጁ በካይዘን የአደረጃጀት ፍልሰፍናን ተግባራዊ እንዲያደርጉ በክልሉ ከተመረጡ 5 ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች መካከል አንዱ እንደሆነ ተናግረዉ በሁሉም የስልጠና ማዕከል የካይዘን የአሰራር ስርአት ተግባራዊ ማደረጋቸዉም አብራርተዋል።

ኮሌጁ እንደ ሀገር የምስራቅ አፍሪካ የካይዘን አዋርድ ተወዳዳሪ በመሆኑንና እስካሁን በተከናወኑ ተግባራትም አበረታች ውጤት ማስመዝገቡን ቡድኑ ባደረገው የመስክ ጉብኝት ማረጋገጥ እንደቻለ ገልፀዋል ።

የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽኑን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ለኢንተርፕራይዞች በሚያጋጥመቸው ችግር ላይ መሠረት ያደረገ ተከታታይነት ያለው ውጤታማ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል ።

በኮሌጁ የመጀመርያ ቀን የስልጠና ክፍለ ጊዜ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ኃላፊ ፣የኮሌጁ አሰልጣኞች ፣የኮሌጁ የቦርድ አመራሮችና የአስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል፡፡

የመማር ማስተማሩን ስራ በይፋ ያስጀመሩት የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዱ አህመድ የ2015 ዓ.ም በክልሉ ያሉ ኮሌጆች ወጥ በሆነ ቀን የዓመቱን ስልጠና መጀመር እንዳለበት በተቀመጠው መሰረት በዛሬ ዕለት የቡታጀራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን ጨምሮ በዞኑ በሚገኙ 11 ኮሌጆች በየፋ ተጀምሯል ብለዋል።

ኮሌጆች ለስልጠና የበለጠ ምቹና ሳቢ ለማድረግ በክረምት ወራት ጥገና የሚያስፈልጋቸውን በመጠገን፣ የኮሌጆች ግቢ በአረንጓዴ ውብ የማድረግ፣ቦርዶችንና ሌሎች አደረጃጀቶችን በማጠናከርና ሌሎች ሰፊ የቅድመ ዝግጀት ስራ መሰራቱን አስታዉሰዋል ።

በሁሉም ኮሌጆች እየገጠመ ያለውን የሠልጣኝ ቁጥር ማነስ ችግር ለመቅረፍ ወጣቶች በመካከለኛ ፣በማታ፣በአጫጭርና በመደበኛው ፕሮግራም ስልጥነው ብቁና ተወዳዳሪ በመሆን ተጠቃሚ እንዱሆኑ የአስተሳሰብና የግንዛቤ ለውጥ እንዲመጣ ሀሉም ባለድርሻ በጋራ መረባረብ አለበት ብለዋል።

የቡታጅራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከተመሠረተ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረው ቢሆንም በሚጠበቀው ልክ ውጤት ማስመዝገብ አለመቻሉን የገለፁት ኃላፊው አቶ አብዱ አሁን ላይ በተቋሙ በአይ ሲቲና በሌሎች የስልጠና ዘርፎች የተሻለ ዉጤት እንዲመጣ በ38 ሚሊየን ብር ወጪ የተለያዩ ግብቶች የማሟላት ስራ ከፌደራልና በሌሎች ባለድርሻ አካላት መሠራቱን አመላክተዋል።

አሁን ላይ በኮሌጁ የተጀመሩ የካይዘን ፍልስፍና ትግበራ ፣በቴኖሎጂ ሽግግር እና ሌሎች መልካም ጀማሮዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል ኮሌጁ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚመለከታቸው አካላት የጋራ ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል።

የቡታጀራ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አማረ አለሙ በበኩላቸዉ የኮሌጁን የመረጃ ስርዓት ለማዘመን በስራና ክህሎት ሚኒስትር ከ38 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገመት የአይ ሲቲ ግብዓት ድጋፍ በቀጣይ በዘርፉ የተሻለ ብቃት ያለው የሠው ሀይል ለማፍራት ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።

በቀጣይ በኮሌጁ የተሻለ ወጤት እንዲመጣ ለማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ወሳኝ እንደሆነም ያብራሩት ምክትል ከንቲባዉ እንደ ከተማ አስተዳደር የሚጠበቅበትን ሁሉ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገለፀዋል።

በኮሌጁ አግኝተን ካነጋገርናቸው መካከል አሰልጣኝ አቶ ከማል ጀማልና ሠልጣኝ አቶ ተመስጌን ብራቱ በሠጡት አሰተያየት የ2015 ዓ.ም የኮሌጁ ስልጠና በጊዜ መጀሩ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል ።
መምህራን አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ ሙሉ ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *