ባለፉት 30 ቀናት ከ1 መቶ 40 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡም የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያዉ በ90 ቀናት ዉስጥ 435 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ እንደሆነም ተመልክቷል።

ህብረተሰቡ በተለያዩ አካባቢዎች የሚያነሳቸዉን የልማትና የመልካም አስተዳድር ችግሮች ለመቅረፍ ግብር በወቅቱ መሰብሰብና መክፈል ይገባል።

የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ አብዱ አህመድ የ90 ቀናት ልዩ እቅድ አፈፃፀም አስመልክተን ለጠየቅናቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ እንዳሉት በመምሪያዉ የ90 ቀናት እቅዱን ለማሳካት በቅንጅት እየተሰራ ሲሆን በዚህም በመጀመሪያዎቹ 30 ቀናት 140 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር መሰብሰባቸዉን ገልፀው በባለፉት አስር ወራት 1 ቢሊየን 467 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ እንደቻሉም አስታዉሰዋል፡፡

መምሪያው በበጀት ዓመቱ ከተለያዩ የገቢ አማራጮች 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ተግባር የገባ ቢሆንም የገቢ አቅምና የመልማት ፍላጎት መሰረት በማድረግ እቅዱን በመከለስ ከ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዶ ከመቼዉም ጊዜ በላይ አጽዕኖት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ በተለያዩ መድረኮች የሚያነሳቸዉ የልማትና የመልካም አስተዳድር ጥያቄ ለመቅረፍ የ90 ቀናት እቅድ ታቅዶ ልዩ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንና በ90 ቀናት ለመሰብሰብ ከታቀደው 435 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ውስጥ ባለፉት 30 ቀናት ጊዜ ዉስጥ 140 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በመሰብሰብ እንደተቻለም ገልፀዋል።

በተሻሻለው የገቢ እቅድ መሰረት በበጀት ዓመቱ ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤቶች ገቢ ብር 1 ቢሊየን 780 ሚሊየን ለመሰብሰብ ታቅዶ በባለፉት 10 ወራት 1 ቢሊየን 467 ሚሊየን ብር በመሰብሰብ የተቻለ ሲሆን ከ10 ወሩ እቅድ አንፃር 99 ከመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።

በወሩ ዉስጥ ለ8 ግብር ከፋዮች ቅሬታ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በ10 ወር ከቀረቡ 197 ቅሬታዎች መካከል 188ቱ ምላሽ መሰጠቱም አመላክቸዋል።

ይህንኑ አፈፃፀም ሊመዘገብ የቻለው ተቋሙን በሰው ሀይልና በእውቀት ከማጠናከር ጀምሮ የገቢ ፊዚካል ስራዎች በአግባቡ ለመፈፀም የተሻለ ጥረት እያደረጉ ሲሆን ለንግዱ ማህበረሰብ የተፈጠረው ጠንካራ የግንዛቤ ስራ እንዲሁም ማንኛውም ነጋዴ ግብርን ሲከፍል አምኖበት እንዲከፍል የሚያስችል አሰራር በመዘርጋቱ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

የሚሰበሰበው የመንግስት ገቢ በየአካባቢው የህዝቡ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚፈቱበት፣ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች እልባት የሚያገኙበት፣ በየአካባቢው ተጀምረው ያላለቁ ፕሮጀክቶች በገንዘብ እጥረት እንዳይስተጓጎሉና የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ግንባታቸዉ አልቆ ለአገልግሎት እንዲዉሉ የሚደረግበት እንደሆነም ገልፀው ።

ለዚህም ስኬት ባለድርሻ አካላትና መላው ማህበረሰብ ትክክለኛ የመንግስት ገቢ ተሰብሰሰቦ ወደ ልማት እንዲቀየር በግብይት ወቅት ደረሰኝ ጠይቆ ከመቀበል ጀምሮ ከገቢ ተቋም ጎን በመሆን ለተግባራዊነቱ ርብርብ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ታክስ መክፈል የእድገትና የኢኮኖሚ መሰረት በመሆኑ ማንኛውም ግብር ከፋይ ግብሩን በታማኝነት በመክፈል ሀገራዊ ግዴታውን እንዲወጣ ጠይቀዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ፡፡

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *