ባለፉት አመታት በተከናወኑ የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ከማሳደጉ ባሻገር በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ ።

ዞናዊ የ2014 ዓመተ ምህረት የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ በጌታ ወረዳ በቋንጤ ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል።

በተፋሰስ እወጃዉ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊና የግብርና ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አክሊሉ ካሳ እንደተናገሩት ከ 2003 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለ11 ተከታታይ ዓመታት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ተግባር በተደራጀ መልኩ በመምራት በርካታ ውጤት ተመዝግቧል።

የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ዋና አላማ ግብርናችንን ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ በተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ላይ የተመሰረተ መስኖን ማስፋፋት የአፈርን ለምነትና እርጥበት በማሻሻል የሰብል ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ አንደሆነም ተናግረዋል።

የመኖ ልማትና አቅርቦት በማሳደግና የእንስሳት ልማት ውጤታማነትን ለማሻሻል የስነ ህይወት ልማትና ጥበቃ በትኩረት ለመፈፀም የተቀናጀ የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ስራ አጋዥ እንደሆነም አብራርተዋል።

ከተሳትፎ አንፃር የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ የሴቶች ተሳትፎ 30 በመቶ የወጣቶች 15 በመቶ ቀሪው በአርሶአደሩ በመሸፈን ዝግጅቱ ሳይቋረጥ ለ35 ተከታታይ ቀናት ይቆያል ሲሉ አቶ አክሊሉ ገልፀዋል።

የጌታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቅባቱ ተሰማ እንደገለፁት እንደ ወረዳው የተፋሰስ ልማት ስራ የተለያዩ የስነ-አካላዊና ስነ ህይወታዊ ስራዎች መሰራት ከጀመረ በኋላ አበረታች ዉጤት እየተመዘገበ እንደሆነም አስረድተዋል።

በተፋሰስ የለሙ ቦታዎች በተቀናጀ መልኩ የእንስሳት እርባታና የሰብል ልማት ስራ ተከናውኖባቸዋል የሚሉት አቶ ቅባቱ በዚህም በርካታ አርሶ አደሮች ተጠቃሚነት መረጋገጡን ገልጸዋል።

በዘንድሮው በወረዳው በ16 ንዑስ ተፋሰስ በ 5 ሺህ 6 መቶ ሄክታር መሬት በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ለማልማት ግብ ተጥሎ እየተሰራ ነው የሚሉት አስተዳዳሪው አርሶ አደሮቹ በመክፈቻው ያሳዩትን ተነሳሽነት ተግባሩ እስኪጠናቀቅ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

ወጣት መኑር አባስ እና አርሶ አደር አብድል ጀሊል ፈረጃ የቋንጤ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ ይህ ተግባር ከተጀመረ ወዲህ ከዚህ በፊት በጎርፍ ይታጠብ የነበረው አፈር ማዳን ችለናል ብለዋል።

ከአፈርና ውሃ ጥበቃው በተጨማሪ ለተሻሻለ የእንስሳት ዝርያ መኖ በማምረት ተጠቃሚ መሆናቸውን አርሶአደረቹ አክለው ገልፀዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *