ባለፉት አመታት በተከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የአፈር ለምነት ከማስጠበቁም ባለፈ ምርትና ምርታማነታቸው እንዳሳደገላቸው የቸሃ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ።

የ2016 ዓ.ም የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በቸሃ ወረዳ በየሰሲየና ቋሸ ቀበሌ ተጀምሯል።

በወረዳው በዘንድሮ አመት 8ሺህ 1መቶ ሄክታር መሬት በአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እንደሚለማ ተመልክቷል።

አቶ መስቀሉ በርሄ እና ወይዘሮ ይስሬሽ ሰክት የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ሲያከናውኑ አግኝተን ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች ናቸው።

እንደ አርሶ አደሮቹ ገለጻ በባለፉት አመታት በተከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የአፈር ለምነት ከማስጠበቁ ባለፈ ምርትና ምርታማነታቸውን እንዳሳደገላቸው ገልጸዋል።

ከዚህም ባለፈ ከዚህ ቀደም ከአገልግሎት ዉጪ የነበሩ መሬቶች አገግመው የተለያዩ ሰብሎችን በመዝራት ውጤታማ እንደሆኑ አርሶ አደሮቹ አመላክተዋል።

አርሶ አደሮቹ አክለውም መሬት ለቀጣይ ትውልድ የሚያስተላልፉት ሀብት በመሆኑ በተገቢው መንከባከብና መጠበቅ ላይ ሁሉም በትኩረት እንዲሰራም መክረዋል።

አርሶ አደሮቹ ያገኙትን ጥቅምና ያላቸውን ግንዛቤ ይበልጥ በመጠቀም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ከወል መሬት በተጨማሪ በጓሮአቸውም አጠናክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የቸሃ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ሽምነሳ እንዳሉት በወረዳው ከዚህ ቀደም በተከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ከዚህ ቀደም ተጎድተው ከምርት ውጪ የነበሩ መሬቶች ምርት እንዲሰጡ፣ የአፈር ለምነት እንዲጠበቅ ከማድረጉም ባለፈ ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ረገድ ሚናው የላቀ መሆኑን አንስተዋል።

እንደ ዋና አተዳዳሪው ገለጻ ከዚህ ቀደም በተሰራው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ወጣቶችን በማደራጀት የተለያዩ የስራ እድል በመፍጠር በመኖና የተለያዩ ሰብሎችን በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን አቶ ጥላሁን ገልጸዋል።

የወረዳው የህብረተሰብ ክፍሎች የተፋሰስ ጥቅም በመረዳትና ያላቸውን ግንዛቤ በመጠቀም በየአመቱ በተጠናከረ መልኩ እየሰሩ እንደሚገኙ አንስተው በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ምክንያት መሬቱ እንዳይሸረሸር ለማድረግ በየአመቱ የስነ ህይወታዊ ስራ እንደሚሰራንና በዚህም በተሰራው ስራ ችግኞቹ ወደ ደንነት ተቀይሯል ብለዋል።

አርሶ አደሮቹ በወል መሬት ከመስራት ባለፈ በጓሮአቸው እንደሚሰሩ ጠቅሰው የተሰሩ ቦታዎች ከሰውና ከእንሰሳት ንክኪ ነጻ ለማድረግ አጥር በማጠር መንከባከብ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የቸሃ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትልና የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙንጠቃ ናስር በወረዳው በዘንድሮ አመት በ38 ንዑስ ተፋሰስ 8ሺህ 1መቶ ሄክታር መሬት በአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እንደሚለማ አመላክተዋል።

በዚህም 48 ሺህ 287 የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉም ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ተጎድተው የነበሩ መሬቶችን በተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በመስራት ተሸርሽሮ ይሄድ የነበረውን ለም መሬት እንዲጠበቅ ከማድረጉም ባለፈ የአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነት ማሳደጉንም አመላክተዋል።

የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ መስራት የአካባቢው ስነ ምህዳር ከማስተካከሉ ባለፈ ሀገራዊ ግድብና መስኖ ፕሮጀክቶች በደለል እንዳይጠቁ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከዚህ በፊት ከስነ አካላዊ ስራ ባሻገር በወረዳው በተሰራው ስራ የስነ ህይወታዊ ስራ በርካታ ቦታዎች አገግመው የተተከሉ ችግኞች ወደ ደንነት መቀየሩ አንስተው በዘንድሮ አመትም ከ12 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=440108594825557&id=100064792596360&mibextid=2JQ9oc

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *