ባለፉት ስድስት ወራት በኢንቨስትመንት፣ በንግድና ገብያ ልማት እንዲሁም በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ በተሰሩ ስራዎች የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ፣የንግድና ገበያ ልማት እና የስራ ዕደል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ሴክተሮች የጋራ ንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተከሄዷል።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዳሉት ባለፉት ስድስት ወራት ሰላምና ጸጥታ ከማስከበር ባለፈ በልማት ስራዎች ፣ በስራ እድል ፈጠራ ፣ በኢንቨስትመንት ፣በንግድና ገበያ ልማት የተሰሩ ስራዎች አበረታች ናቸዉ።

ባለሀብቱ በመሰረታዊነተ እንደ ችግር ያነሱት መሬት ወስደዉ አጥሮ የማስቀመጥና ያለ ማልማት ችግሮች መኖራቸዉም አንስተዉ አለሙ የሚባሉ ባለሀብቶችም ከአርሶአደር ያልተሻለ ስራ ቴክኖሎጂ የማያሸጋግሩ ፣ ለዜጎች የስራ ዕድል የማይፈጥሩ እንዲሁም ጥራት ያለዉ ምርት የማያመርቱ ባለሀብቶች ቁጥር በጣም ከፍተኛ ነዉ ብለዋል።

አቀም ያላቸዉ አልሚ ባለሀብቶች ወደ ዞኑ እየመጡ ስለሆነ መሬት ወስደዉ ወደ ስራ ያልገቡ ባለሀብቶች መሬታቸዉ በመልቀቅ እርምጃ በመዉሰድ ባለን ዉስን መሬት ሀይ ቴክ ለሆኑ ቴክኖሎጂዎች አሰራሩን ጠብቀን ለዉጭ ኤክስፖርት ሊደረጉ የሚችሉ በአጭር ቦታ ላይ ብዙ የስራ ዕድል የሚፈጥሩ ብዙዎችን የሙያ ምርት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚባም አብራርተዋል።

ህገወጥ የንግድ ቁጥጥር በመከላከል የመንገድ ዳር ንግድ በተገቢዉ ማስቆም እንደሚገባና የኮንትሮባንድ ዝዉዉርን ለማስቆም ከመቼዉምጊዜ በላይ በቅንጅት መሰራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

ህዝቡ የሚያነሳዉን የኑሮ ዉድነት ለመቀነሰ በሁሉም ዘርፍ ማምረት እንደሚገባና ያሉ መሬቶች እንዲታረሱ በማድረግ የዋጋ ግሽበቱን በተገቢዉ መከላከል እንደሚገባም አስረድተዋል።

የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ በበኩላቸዉ ለዞኑ ልማትና እድገት የአመራሩ ሚና የጎላ እንደሆነም ተናግረዉ በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣና ለወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር መሬት ተረክበዉ በአግባቡ ያላለሙ ባለሀብቶች እርምጃ መዉሰድና ለሚያለሙ ባለሀብቶች መስጠት ይገባል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ናስር ሀሰን እንዳሉት በዞኑ የተጀመሩየኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪዎች ማስፋፋት ፣የስራ አጦች ልየታና ስራ ፈጠራ የአምራቾችና የሸማቾች ትስስር በመፍጠርና የገበያ ማረጋጋት ስራዎች በተናጠል ከሚደረገዉ ይልቅ ብዙ የሚያስተሳስራቸዉ ተግባርና ዉጤት ያላቸዉ ዘርፎች በመሆናቸዉ በጋራና በተቀናጀ ሁኔታ በመስራት ዉጤት ማምጣት ይገባል።

እንደዞን በኢንቨሰትመንት ዘርፉ መልካም የሚባል ውጤት አሳይቷል ያሉት ሃላፊው በዚዚህም ምርታቸውን ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ ባለሃብቶች ተፈጥረዋልም ብለዋል።

ለባለሃብት ከተላለፈው 1790 ሄክታር የሚጠጋ መሬት ውስጥ ያለማው ከፍተኛ እንደሆነም ተናግረዋል።

ወደ ተግባር የገቡ ባለሃብቶች ተገቢውን ድጋፍ ይደረግላቸዋል ያሉት ሃላፊው በአንፃሩ ቀደም ብለው ከተሰሩ ማስተካከያዎች በተጨማሪ በቀጣይ ወደ ስራ ያልገቡ መሬቶችን ወደ ስራ ለማስገባት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ መላኩ ብርሃኔ እንዳሉት በየደረጃዉ ህዝቡ የሚያነሳዉን የኑሮ ዉድነቱን ለማረጋጋት የሁሉም ሰዉ ርብርብና ጥረት ይጠይቃል።
የንግድ ስርዓቱ በማዘመን ህብረተሰቡ በፍትሃዊነት ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ ይገባል ብለዉ ህገወጥ ንግድ ፣የኑሮ ዉድነት አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ፣ህገወጥ የምርት ክምችትና የኮንትሮባንድ ዝዉዉር ለመቀነስ ከመቼዉም ጊዜ በላይ በቅንጅት ሊሰራበት እንደሚገባም አመላክተዋል።
የጉራጌ ዞን የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሙራድ ያሲን አንዳሉት የስራ አጥነትና የኑሮ ዉድነት የሀገራችን ብሎም የዞናችን ህዜቦች አንገብጋቢ ጥያቄዎች ከመሆኑም ባለፈ ለሰላም ዕጦትና ሀገር ሀገር እንዳይረጋጋ ምክንያት ከሚሆኑ ጉዳዮች አንዱ ነዉ።

በስራ ዕድል ፈጠራ አበረታች ዉጤቶች ያሉ ሲሆን ስራ ፈላጊዎችን አሟጦ ወደ ስራ ያለ ማስገባት ፣በቂ የሆነ የመንግስት ድጋፎች ፣ የግብአት የክህሎትና ድጋፎችን አሟልቶ ያለማቅረብ ጉድለት እንዳለም አመላክተዋል።

በበጀት አመቱ ስራ ፈላጊዎችን ለመመዝገብ ሰፊ ስራዎች መሰራቱም አንስተዉ በዚህም 24 ሺህ 8 መቶ 61 ወንድ እንዲሁም 4 ሺህ 71 በድምሩ 38 ሺህ 9 መቶ 32 መመዝገባቸዉም አስታዉሰዋል።

በመደረኩ የተገኙ አንዳንድ ባለድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየት ህዝቡ የሚያነሳቸዉ የኑሮ ዉድነቱን ለመከላከል ሶስቱም ተቋማቶች እንዲሁም አመራሩ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባም አብራርተዋል።

በኢንቨስትመንቱ ዘርፈ እየተሰተዋለ ያለዉን መነቃቃት በማስቀጠልና በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በመቀረፍ ዉጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባም አንስተዉ መሬት የተረከቡ ባለሀብቶች ቶሎ ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግና በቅንጅት መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

መሬት ወስደዉ ወደ ተግባር ያልገቡ ባለሀብቶች ላይ አስተማሪ እርምጃ መዉሰድ እንደሚገባና በዘርፉ የሚፈለገዉ ዉጤት ማምጣት እንደሚገባም ተናግረዋል።

ትላልቅ አቅም ያላቸዉ ባለሀብቶች ወደ የአካባቢያችን እንዲመጡና እንዲያለሙ በማድረግ የስራ አማራጮችን በማስፋት ለወጣቱ የስራ ዕድል መፍጠር እንደሚገባም አስረድተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሸን መምሪያ ነዉ ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *