ባለፈው አንድ ወር 5 ሺህ 96 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉና ከ36 ሚሊየን ብር በላይ ብድር ማስመለሱም የጉራጌ ዞን የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራዞች ልማት መምሪያ አስታወቀ ።

ባለፉት አመታት ሼድ ወስደዉ ተጠቅመዉ በወቅቱ ካልተመለሱ 208 ሼዶች መካከል እስካሁን በአመቱ 72 ሼዶች ማስመለስ መቻሉም መምሪያው ጠቁመዋል ።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በቅርቡ በከተሞች ከህዝብ ጋር በተደረጉ ውይይቶች ከወጣቱ ስራ አጥነትና የኢኮኖሚ ቸረግር ተያይዞ ሰፊ ጥያቄዎች መነሳታቸው በማስታወስ በታቀደው የ90 ቀን እቅድ መሰረት ችግሮቹን ለመፍታት ምን እየተከናወነ እንደሆነ የመምሪያው ሀላፊ አቶ አበበ አመርጋ ጠይቋል።

እንደ ሀላፊው ገለፃ ህዝቡ በየደረጃው ያነሳቸዉ ከወጣቱ ስራ እድል ፈጠራና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ተያይዞ የተነሱ ጥያቄዎች ለመፍታት የ90 ቀን እቅድ በማቀድ በየደረጃው ከሚገኘው መዋቅር፣ከመምሪያው ማኔጅመንትና ሰራተኞች ጋር መግባባት በመፍጠር ወደ ተግባር መገባቱና ውጤቶችም እየተመዘገበ መሆኑ ገልፀዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት ዜጎች በከተማና በገጠር ወደ ስራ ለማሰማራት የተጣለውን ግብ ለማሳካት ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪ በተቋሙ የ90 ቀናት እቅድ መሰረት ዋና የትኩረት ነጥብ በማድረግ እየተደረገ ባለው ርብርብ በባለፈው አንድ ወር ለ5 ሺህ 96 ዜጎች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን በበጀት ዓመቱ እስካሁን ለ41 ሺህ 59 ዜጎች በቋሚና በጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠር ተችሏል ።

ይህ የ90 ቀናት ዕቅድ አቅዶ ወደ ተግባር ከገባ በኋላ ለ5 ሺህ 96 ዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ሌሎች ወጣቶች ስራ ለመፍጠር 36 ሚሊየን 436ሺህ 134 ብር ብድር ማስመለሳቸዉም አስታዉቀዋል።

በተለያዩ ዓመታት ለወጣቱ የስራ ዕድል ለመፍጠር ተብሎ የተሰራጨው የብድር መመለሻ ጊዜው ደርሶ ያልመለሱ ማህበራት በተገቢዉ በመለየትና በማስመለስ ላልተጠቀመዉ ወጣት ለማስጠቀም በተደረገው ጥረት በበጀት አመቱ እስካሁን 111 ሚሊየን ማስመለስ መቻሉም ጠቁመዋል።

በከተማና በገጠር በአዲስ ተደራጅተው ወደ ስራ ለተሠማሩ ወጣቶች 65 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ብድር መሠራጨቱም አስታዉሰዋል ።

የመንግስት ሼዶች አስተዳደር በአሰራሩ መሠረት ተግባራዊ አለማድረግ ሼዶች ወስደው ተጠቅመው በወቅቱ ያልመለሡ 208 ሼዶች መኖራቸውንና በዚህ ምክኒያት በቅርቡ ከወጣቱና ከህዝቡ በተፈጠሩ መድረኮች ቅሬታዎች መነሳታቸው ገልፀው እስካሁን በአመቱ 72 ሼዶች ማስመለስ እንደቻሉም አብራርተዋል።

በቀጣይ በከተማና በገጠር በተለዩ የግብርና ዘርፎች ወጣቶችን በማሰማራት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የተሻለ የምርት አቅርቦት አንዲኖር በማድረግ አሁን ላይ እንደ ሀገር እየተስተዋለ ያለዉን የገበያ አለመረጋጋት የራሱ በጎ ተፅኖ እንዲያሳድር በትኩረት እንደሚሰራም አመላክተዋል።

ከብድር ስርጭት ፣ከእዳ አመላለስ እንዲሁም ከመስሪያና መሸጫ ቦታ አቅርቦት ተያይዞ እየገጠሙን ያሉ ማነቆዎችን በመፍታት ወጣቱን የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ የጋራ ጥረት ይጠበቃል ብለዋል።

በዘርፉ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ ያጋጠሙ ችግሮቾን በመቅረፍ ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የ90 ቀን እቅድ ትግበራ እና በየደረጃው የሚገኙ የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት በተጀመረው መልኩ በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ ።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *