ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ዘርፍ በመሰማራት እያደረጉት ያለዉ በጎ እንቅስቃሴ አጠናክረዉ መቀጠል እንዳለባቸዉ የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዲስትሪ መምሪያ አስታወቀ፡፡

ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ዘርፍ በመሰማራት እያደረጉት ያለዉ በጎ እንቅስቃሴ አጠናክረዉ መቀጠል እንዳለባቸዉ የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዲስትሪ መምሪያ አስታወቀ፡፡

በጉራጌ ዞን እዣ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ያለበት ደረጃ ጉብኝት ተካሂዷል ።

የጉራጌ ዞኑ ኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊ አቶ ናስር ሀሰን እንደገለፁት የአካባቢ ተወላጅ እና ሌሎችም ባለሀብቶች በዞኑ ላይ ያለዉን የመሬት አማራጮችን ተጠቅመዉ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት በማድረግ ተጠቃሚነታቸዉ በተጨባጭ ማረጋገጥ እየቻሉ ነው ብለዋል ።

የመስክ ምልከታው አላማ በወረዳው በኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች የስራ እንቅስቃሴያቸው ያለበት ደረጃ ተዟዙረው በመመልከት የተሻሉ ስራዎች ለማስቀጠልና ወደ ስራ ያልገቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ስራ እንዲገቡ ለማስቻል እንደሆነም ሀላፊው አመላክተዋል ።

በዞኑ በኢንዱስትሪና በግብርና ዘርፍ ፍቃድ ወስደው ወደ ተግባር ያልገቡ 25 ፕሮጀክቶችን ውል በማቋረጥ 359 ሄክታር ወደ መሬት ባንክ ማስገባታቸው የተናገሩት ኃላፊው ወደ መሬት ባንክ ከገባው ውስጥ ለአልሚ ባለሀብት በማስተላለፍ ወደ ተግባር መገባቱንም አቶ ናስር አስረድተዋል ።

በተለያዩ ዘርፎች መሬት ተረክበዉ ያላለሙ ባለሀብቶች በፍጥነት ወደስራ መግባት እንዳለባቸዉ ያሳሰቡት አቶ ናስር ያላለሙትንም በየደረጃው እየተወሰደ ያለውን የእርምት ርምጅ ተጠጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በበኩላቸው እንዳሉት ኢንቨስትመንት የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገትን በማፋጠንና የዜጎችን የስራ ዕድል በመፍጠር ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና በተለያዩ መልኩ የሚያደርጉት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በወረዳው በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ በተደረጉ ምች ሁኔታዎች በርካታ ባለሀብቶች በተለያየ ዘርፈ በመሰማት ውጤታማ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ያሉት አቶ ዘውዱ ከእነዚህም መካከል በአበባ እርሻ ልማት ፣ በዉሃ ማሸግ ፡ በችቡድ ፋብሪካ ፡ በሆልቲ ከልቸር ፡ ብረት ብረትና ፕላስቲክ ማምረቻ ፋብሪካዎች ተጠቃሾች ናቸው ብለዋል።

እንደወረዳው 63 ኢንቨስትመንቶች ፈቃድ ወስደው የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም መካከል 12 የሚሆኑትን ለረጅም ጊዜ አጥር አጥረው በማስቀመጥና ባለማልማት ውላቸው መቋረጡንም ገልፀዋል።

በቀጣይም መሬት ወስደዉ በሙሉ አቅማቸዉ ወደ ስራ ያልገቡ ባለ ሀብቶች በአፋጣኝ ማልማት እንዳለባቸዉና የማያለሙ ከሆነ መንግስት ተገቢዉን እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነም ገልፀዋል።

በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች በሰጡት አስተያየትም እንደዚህ መሰል ምልከታዎች ጉለቶቻቸውን እንዲቀርፉ ሰፊ እድል የሚፈጥር በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጥል እንዳለበት ተናግረው ሆኖም የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ ለማስቻል ያሚያጋጥማቸው በተለይም የመብራት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች የሚመለከታቸው አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባናል ብለዋል።

በጉብኝቱ በወረዳው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች እየተጎበኙ ሲሆን የማጠቃላይ የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተ ማ የጆካ ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ላይ ተካሂዷል።

በእለቱም የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ መምሪያ ፡ የእዣ ወረዳ ኢንቨስትመንት ኮሚቴ አመራሮች እንዲሁም በወረዳው በኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የዘገበው የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *