ቡና ላይ የምርምር ስራዎችና ኤክስቴንሽን አቀናጅቶ መስራት ባለመቻሉ በሀገሪቱ የቡና ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እንዳልተቻለ ተገለጸ፡፡

ቡና ላይ የምርምር ስራዎችና ኤክስቴንሽን አቀናጅቶ መስራት ባለመቻሉ በሀገሪቱ የቡና ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እንዳልተቻለ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ የቡና ሳይንስ ማህበር በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሲያካሂድ የነበረው አመታዊ ኮንፈረስ ውጤታማ በሆነ መልኩ ተጠናቋል፡፡

ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ኮንፈረስ ማጠቃለያ የተለያዩ ምሁራን እንዳሉት በቡና ላይ የሚካሄዱ የምርምር ስራዎችና ኤክስቴንሽን አቀናጅቶ መስራት ባለመቻሉ በሀገሪቱ የቡና ምርትና ምርታማነት በሚፈለገው ልክ ማሳደግ አልተቻለም፡፡

በምርምር ማዕከል ውጤታማነታቸውን የተረጋገጡ የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎች በማላመድ አርሶ አደሮች እንዲጠቀሙ የቡና ኢክስቴንሽን አደረጃጀት መዋቅር እስከታች እንዲዋቀር ምክረ ሀሳብ ለሀገሪቱ ፖሊሲ አውጪዎች እንዲቀርብ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ቡና የማያመርቱ አውሮፓውያን ቡና ከኛ ገዝተው ተጨማሪ እሴት ጨምሮበት በተሻለ ዋጋ እየሸጡ ከኛ በተሻ ተጠቃሚ መሆናቸው የገለጹት የኮንፈረሱ ተሳታፊዎች በቀጣይ በማዳቀል ዝርያ በማሻሻል ምርትና ምርታማነትና ጥራት ማሳደግ እንዲሁም ተጨማሪ እሴት በመጨመር ሀገሪቱ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንድትሆን ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ብቻ ሳይሆን የቡና የምርምር ስራዎች በመሸጥ እና ቱሪዝም በማስፋት ገቢ ማግኘት እንደምትችል የኮንፈረሱ ተሳታፊ ምሁራን አመላክተዋል፡፡

ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ኮንፈረንስ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የኮንፈረሱ ተሳታፊዎች በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በሸብራደን ቀበሌ በአርሶ አደር ሳህሌ ሀይሌ በመልማት ላይ የሚገኝ የቡና ችግኝና ማሳ የመስክ ምልከታ እና የጉራጌ የአባቶች የምህንድስና ጥበብ ውጤት የሆነው ውብ ጀፎረ መንጠር ቀበሌ ኢሰፋጣጥ መንደር በማስጎብኘት ተጠናቋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *