በ360 ሚሊየን ብር የ8.3 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ አስፉልት መንገድ ግንባታ ለማስጀመር ከኢትዮጲያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር የዉል ፊርማና የሳይት ርክክብ መደረጉን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ ።

የከተማው ህዝብ በየደረጃው የሚያነሳቸው የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት እየተሰራተ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ገልፀዋል።

ከገብርኤል ቤተክርስቲያን እስከ ወልቂጤ ምክር ቤት ፣ከሰላም ካፌ እስከ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ቅርንጫፍ ፣ከዋና ማዘጋጃ እስከ ማራኪ ካፌ የሚሸፍን የአስፓልት መንገድ ግንባታ በሁለት አመት ይጠናቀቃልም ተብሏል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ገብረመስቀል በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት ለበርካታ አመታት ህብረተሰቡ ሲያነሳው የነበረው የውስጥ ለውስጥ የተለዋጭ አስፋልት መንገድ ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል በሁሉም ክፍለ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ለማስገንባት የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ነው ብለዋል።

ከገብርኤል ቤተክርስቲያን እስከ ወልቂጤ ምክር ቤት ፣ከሰላም ካፌ እስከ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ቅርንጫፍ ፣ከዋና ማዘጋጃ እስከ ማራኪ ካፌ የሚሸፍን በአጠቃላይ የ8.3ኪሎ ሜትር የወስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ በ360 ሚሊዮን ብር በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ከኢትዮጲያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር የዉል ፊርማና የሳይት ርክክብ መፈፀሙን አብራርተዋል ።

ተቋራጩ እንደ ሀገር ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የመጨረስ ልምድ ያለው በመሆኑ በከተማው ቀድሞ ተጀምረው የተጓተቱ ፕሮጀክቶችን በሚያካክስ መልኩ እንደሚሠራ ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል አቶ እንዳለ።

ከንቲባው አክለውም የመንገድ ስራዉ በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቅ ከመንግስትም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ለሚነሱ የቦታ ወሰንና ሌሎች ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲቻል የአካባቢው ህብረተሠብ ያለበት ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሰራ መገባቱንም ተናግረዋል ።

የኢትዮጲያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኢ/ር,ዮናስ አያሌው በርክክቡ ስነ ሰርዓት ወቅት እንደገለጹት ከወሰን ማሰከበር፣ ለመንገድ ግንባታው ከአካባቢው የሚፈለጉ የግብዓት አቅርቦት እጥረትና መሰል ችግሮች ካልገጣማቸው በስተቀር ውል ከገቡበት ጊዜ አስቀድመው ለመጨረስ ድርጅቱ አስፈላጊውን የሰው ኃይል፣ የግብዓትና ሌሎችም የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል ።

ቀድሞ የተጀመረው 1ነጥብ 7ኪሎ ሜትር ከአደባባይ እስከ ኮሎጅ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ከወሰን ማስከበር ጋር፣ በአለምገና ዲስትሪክት በነበረው የውስጥ ችግርና በሌሎችም ምክንያቶች መንገዱ ከሚገባው በላይ መዘግየቱን ገልፀው።

አሁን ላይ ድርጅቱ ባደረገው ሪፎርም የ8 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታው ባጠረ ጊዜና በተሻለ ጥራት አጠናቆ ለማስረከብ ከፋተኛ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል።

ከኢትዮጲያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የወልቂጤ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ተክሌ ከፍላይ ቀድሞ የተጀመረው የአንድ ነጥብ ሰባት ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ከ95 ከመቶ በላይ መከናወኑንና ቀሪ ስራው ባጭር ገዜ ለመጨረስ በትኩረት አየተሠራ ነው ብለዋል።

አዲሱ የ8.3ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ስራ ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ ይገባል ብለዋል።

በርክክቡ ወቅት አስተያየታቸውን ከሰጡን የከተማው ነዋሪዎች መካከል አቶ ደጉ አለሙ እና ሐምዲሣ አለሙ መንገዱ ባለመሰራቱ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች እየተጋለጡ እንደነበረ ገልፀው ከለውጡ ወዲህ የከተማው አስተዳደር የጀመራቸው የመንገድ ልማት ስራዎች አበረታች በመሆኑ በሁሉም ዘርፎች ተጠናክሮ ሊቀጠል ይገባል ብለዋል።

የመንገድ ግንባታ ስራዉ እንደ ቀድሞ ፕሮጀክቶች ሳይዘገይ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ መንግስት ተገቢውን ክትትል እንዲያደርግና እነሱም የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ።

በዝግጅቱ የከተማው አመራሮች ፣የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መሳተፍቸውና ግንባታ ላይ ያሉ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *