በ30 ሚሊዮን ብር 2 የጥልቅ ውሃ ቁፋሮ ፕሮጀክቶችን ግንባታ እየተፋጠነ እንደሚገኝ የጉራጌ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ አስታወቀ።

የወልቂጤ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ
መምሪያው በአበሽጌ ወረዳ ጣጤሳ ቀበሌ እየተገነቡ የሚገኙት የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታ ሲጠናቀቁ የከተማዋ የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀርፍም ተገልጿል ።
የጉራጌ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ምክትል ኃላፊና የመጠጥ ውሃ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ዮሐንስ መሰለ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት የዞኑ የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ዝቅተኛ መሆኑን ጠቁመው ይህም ችግር ለመቅረፍ ሰፋፊ ፕሮጀክቶች ለማስገንባት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
አክለውም ከዚህ በፊት ለወልቂጤ ከተማው ህዝብ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የውሃ ፕሮጀክት ከከተማው የህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ ከተጠቃሚው ህብረተሰብ ፍላጎት አንፃር ባለመመጣጠኑ ችግሩ ለመቅረፍ በእቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
በዚህም መምሪያው አሁን ላይ በከተማው የሚስተውዋለውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር በጊዜያዊነት ለመቅረፍ ሁለት ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፍሮ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የገለፁት አቶ ዮሐንስ ችግሩንም በዘላቂነት ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ጥናቶችን እየተጠኑ ነው ብለዋል።
የከተማው የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር በጊዜያዊነት ለመቅረፍ በ30 ሚሊየን ብር ወጪ በአበሽጌ ወረዳ ጣጤሳ ቀበሌ 2 የውሃ ፕሮጀክት እየተገነቡ መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል።
እንደ አቶ ዮሐንስ ገለፃ በጣጤሳ የሚገነቡት ፕሮጀክቶች ከእያዳንዱ 20 ሊትር በሰከንድ ያስገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም በመግለፅ።
ፕሮጀክቶቹ 300 ሜትር ጥልቀት ለመቆፈር ውል የተገባ ሲሆን እስካሁን የጣጤሳ አንድ የንፁህ መጠጥ ውሃ የፕሮጀክት 240 ሜትር ሲደርስ የጣጤሳ ሁለት ደግሞ 164 ሜትር ላይ መሆናቸውን የተናገሩት ኃላፊው ፕሮጅክቶቹም በተያዘላቸው ጥራትና ፍጥነት እየተከናወኑ መሆኑንም አስረድተዋል።
አያይዘውም የውሃ ፕሮጀክቶቹ ተጠናቆ ለህብረተሰቡ በአጭር ጊዜ ተደራሽ ለማድረግ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ውሃና ማዕድን ኤነርጂ መምሪያ የጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ ፕሮጀክት ሳይት ሱፐርቫይዘር አቶ ረኢስ አስፋው በበኩላቸው ከደቡብ ክልል ውሃ ስራዎች ጋር በተገባው ውል መሰረት የፕሮጀክቶቹ የቁፋሮ አፈፃፀም በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ፕሮጀክቶቹም በከፍተኛ ጥራትና በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ በቁርጠኝነት እየሰሩ መሆኑንም አቶ ረኢስ አስፋው ገልፀዋል።
አክለውም የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶቹ ተጠናቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አክላትና ህብረተሰቡ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።

  • አካባቢህን ጠብቅ!
  • ወደ ግንባር ዝመት!
  • መከላከያን ደግፍ!
    በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
    Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
    Website:- https://gurage.gov.et
    Telegram:- https://t.me/comminuca
    Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *