በ2017 የትምህርት ዘመን በዞኑ በሚገኙ በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች በቅድመ መደበኛ እና በአንደኛ የክፍል ደረጃ የጉራጊኛ ቋንቋ ትምህርት የሚሰጥ በመሆኑ ተቋማቱ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ገለጸ።

መምሪያው የጉራጊኛ ትምህርት መጽሀፍቶች ለማዳበር ለጉራጊኛ ትምህርት መምህራና ባለድርሻ አካላት ሲሰጥ የነበረው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናና የምክክር መድ

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማርያም እንዳሉት በዞኑ የጉራጊኛ ቋንቋ በስርአተ ትምህርት በማካተት የተጀመረው ስራ ይበልጥ ለማጠናከር ለመምህራን እና ለባለድርሻ አካላት ስል

ስልጠናው የ


መምሪያው የጉራጊኛ ትምህርት መጽሀፍቶች ለማዳበር ለጉራጊኛ ትምህርት መምህራና ባለድርሻ አካላት ሲሰጥ የነበረው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናና የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ።

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማርያም እንዳሉት በዞኑ የጉራጊኛ ቋንቋ በስርአተ ትምህርት በማካተት የተጀመረው ስራ ይበልጥ ለማጠናከር ለመምህራን እና ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናው የጉራጊኛ ቋንቋ መምህራን አቅም ከማጎልበት ባለፈ የቋንቋ ቴክኒክ ኮሚቴ በመስክ ምልከታው ወቅት የተመለከቷቸው ጠንካራ ጎኖች ለማስቀጠልና ደካማ ጎኖች በማረም በቀጣይ ስራው ውጤታማ ለማድረግ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

በ2016 የትምህርት ዘመን የጉራጊኛ ቋንቋ በተመረጡ 18 ትምህርት ቤቶች ለአንደኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሰጥ እንደነበረ ገልጸው በ2017 የትምህርት ዘመን በ401የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለአንደኛ ክፍልና ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች እንደሚሰጥ አስረድተዋል።

እንደ አቶ መብራቴ ገለጻ በዞኑ በሚገኙ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች የጉራጊኛ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት አይነት ለመስጠት ግብ ተጥሎ እየተሰራ ሲሆን በ2017 የትምህርት ዘመን በ18 ት/ቤቶች የሁለተኛ ክፍል የሙከራ ትምህርት ይጀመራል ነው ያሉት።

በቀጣይ አመት በዞኑ በሁሉም በመንግስትና በግል ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች የጉራጊኛ ቋንቋ ትምህርት እንደሚጀመር የገለጹት አቶ መብራቴ ተቋማቱ የመምህራንና የመጽሐፍት እጥረት እንዳይገጥም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

ስልጠናው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመው በቀጣይ በዞኑ የሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ባላቸው ተማሪና ትምህርት ቤት ልክ መምህራን በማዘጋጀት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የጉራጊኛ ቋንቋ በማበልጸግ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገገር መምህራን፣ ወላጆች፣ ባለሀብቶች እና ሙህራን እንዲሁም የትምህርት ተቋማት የላቀ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋና ስነጽሁፍ ትምህርት ክፍል ተመራማሪና መምህር ካሚል ኑረዲን በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የጉራጊኛ ቋንቋ ትምህርት ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየሰራ ይገኛል።

የጉራጊኛ ቋንቋ ትምህርት በስርአተ ትምህርት ተካቶ ከተጀመረ ወዲህ ሁሉም ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት የተሻለ ደረጃ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ቋንቋው የትምህርትና የሚዲያ ቋንቋ ለማድረግ የተጀመረው ስራ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ ጠቁመው ባለድርሻ አካላት የየበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

መምህርት ታሪኳ መለሰ በአገና 01 ትምህርት ቤት መምህርት ሲሆኑ ሸምሱ ሞሄ ደግሞ በጉንችሬ ቆጭራ ትምህርት ቤት የጉራጊኛ ቋንቋ መምህር ናቸው።

መምህራኑ በስልጠናው በቂ ግንዛቤ እንዳገኙ ጠቁመው በዚህም ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው በቋንቋው እድገት ላይ አሻራቸው ለማኖር በትኩረት እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም ትውልዱ በአፍ መፍቻ ቋንቋው ባለመማሩነሰ ቋንቋው ባለማደጉ ቁጭት ያድርባቸው እንደነበር ያነሱት ሰልጣኞቹ ከቅርብ አመታት ወዲህ የዞኑ መንግስት ለቋንቋው ማደግ ትኩረት በመስጠቱ በትምህርት ቤቶች እየተሰጠ ያለው ስራ ማጠናከር ይገባል ብለዋል ሲል የዘገበው የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በ2016 የትምህርት ዘመን የጉራጊኛ ቋንቋ በተመረጡ 18 ትምህርት ቤቶች ለአንደኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሰጥ እንደነበረ ገልጸው በ2017 የትምህርት ዘመን በ401የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለአንደኛ ክፍልና ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች እንደሚሰጥ አስ

እንደ አቶ መብራቴ ገለጻ በዞኑ በሚገኙ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች የጉራጊኛ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት አይነት ለመስጠት ግብ ተጥሎ እየተሰራ ሲሆን በ2017 የትምህርት ዘመን በ18 ት/ቤቶች የሁለተኛ ክፍል የሙከራ ትምህርት ይጀመራ

በቀጣይ አመት በዞኑ በሁሉም በመንግስትና በግል ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች የጉራጊኛ ቋንቋ ትምህርት እንደሚጀመር የገለጹት አቶ መብራቴ ተቋማቱ የመምህራንና የመጽሐፍት እጥረት እንዳይገጥም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እን

ስልጠናው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመው በቀጣይ በዞኑ የሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ባላቸው ተማሪና ትምህርት ቤት ልክ መምህራን በማዘጋጀት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው ተ

የጉራጊኛ ቋንቋ በማበልጸግ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገገር መምህራን፣ ወላጆች፣ ባለሀብቶች እና ሙህራን እን

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋና ስነጽሁፍ ትምህርት ክፍል ተመራማሪና መምህር ካሚል ኑረዲን በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የጉራጊኛ ቋንቋ ትምህርት ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እ

የጉራጊኛ ቋንቋ ትምህርት በስርአተ ትምህርት ተካቶ ከተጀመረ ወዲህ ሁሉም ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት የተሻለ ደ

ዩኒቨርሲቲው ቋንቋው የትምህርትና የሚዲያ ቋንቋ ለማድረግ የተጀመረው ስራ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ ጠቁመው ባለድርሻ አካላት የየበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅ

መምህርት ታሪኳ መለሰ በአገና 01 ትምህርት ቤት መምህርት ሲሆኑ ሸምሱ ሞሄ ደግሞ በጉንችሬ ቆጭራ ትምህርት ቤት የጉራጊኛ ቋንቋ መምህር ና

መምህራኑ በስልጠናው በቂ ግንዛቤ እንዳገኙ ጠቁመው በዚህም ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው በቋንቋው እድገት ላይ አሻራቸው ለማኖር በትኩረት እ

ከዚህ ቀደም ትውልዱ በአፍ መፍቻ ቋንቋው ባለመማሩነሰ ቋንቋው ባለማደጉ ቁጭት ያድርባቸው እን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *