በ2015 ዓ.ም በዞኑ ከተለያዩ የገቢ አርዕስቶች ከ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡም የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ።

ሰኔ 19/2015 ዓ.ም

በ2015 ዓ.ም በዞኑ ከተለያዩ የገቢ አርዕስቶች ከ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡም የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ።

“ግብር ለሀገር ክብር “‘በሚል መሪ ቃል ከየካቲት 2015 ዓ.ም እሰከ የካቲት 2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው የገቢ ንቅናቄ ስራ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ።

ግብር በወቅቱና በአግባቡ በመክፈል በዞኑ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች በተገቢዉ ማስቀጠል ይገባል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በእለቱ ተገኝተዉ እንዳሉት ለአንድ ሀገር እድገትና ልማት ለማፋጠን ግብርና ታክስ በአግባቡ በመሰብሰብ እና የተሰበሰበዉ ግብር ለታለመለት አላማ ሲዉል ነዉ።

ግብር መክፈል ለሀገሬ ክብር ነው በማለት በታማኝነት ግብራቸውን በመክፈል ግንባር ቀደም ለሆኑ ግብር ከፋዮችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

እንደ መንግስት የህብረተሰቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የማሰፈፀም አቅም ለማሳደግ ግብርን በአግባቡ መሰብሰብ ለሁለንተናዊ እድገት ዋስትና ነዉ ብለዋል።

የህዝቡ የልማት ፍላጎት ለማሟላት በዞኑ በሁሉም ዘርፍ የተጀመሩ የልማት ስራዎች የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በዞኑ የሚስተዋለዉ የታክስ ስወራና ማጭበርበር በማስቆም መሠብሠብ የሚጠበቀዉን ግብር መሰብሰብ በአግባቡ እንደሚገባም አመላክተዋል።

አክለዉም አቶ ላጫ ዜጎች ለከፈሉት ግብር ደረሰኝ የመቀበል ባህላቸዉ ማሳደግ እንዳለባቸዉና ታክስ ማጭበርበር በሀገር ልማት የሚያደርሰው ጫና ከፍተኛ በመሆኑ ይህንን ለማስቀረት በጋራ መረባረብ ይገባል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙራድ ረሻድ እንዳሉት መንግስት የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችለውን የወጪ ፍላጎት ለመሸፈን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ ይገባል።

በዞኑ ኢኮኖሚ የሚያመነጫቸው የገቢ አማራጮችን አሟጦ በመጠቀም የዞኑን ገቢ ለማሳደግ በተሰራው ስራ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉም አስታዉቀዋል።

ይሁን እንጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የዞኑ የወጪ ፍላጎት ለሟሟላትና የበጀት እጥረት ለመቅረፍ ብዙ ስራ መስራት ይጠይቃል ያሉት ሃላፊው በተለይም የታክስ ስወራና የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመከላከል በትኩረት መሰራት እንዳለበትም አብራርተዋል።

በበጀት አመቱ ከ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ እስከ አሁን ባለው ሂደት ከ2ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 93 በመቶ ማሳካት መቻሉን አቶ ሙራድ ገልፀዋል ።

በ2016 በጀት አመት በዞኑ ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱን የገለፁት ሀላፊዉ ይህንን ለማሳካት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር፣ታማኝ ግብር ከፋዮች ማበረታታትና ለግብር ከፋዩ ህብረተሰብ በታክስ ህጎች ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

እንደ መንግስት የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስፈልገዉን ወጪ ለመሸፈን ገቢ ቁልፍ ሚና ይጫወታል ብለዋል ።

በቀጣይ ጀት አመት ተቋሙ 3 ቢሊየን 47 ሚለየን 9መቶ 82 ሺህ 6መቶ 82 ብር ገቢ ለመሰብሰብ ግብ ተጥሏል ብለዋል።

በመጨረሻም በዞኑ የሚገኙ ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮችና ለአጋር የልማት ድርጅቶች እውቅና መሰጠቱም ታዉቋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *