በ2014 ዓመተ ምህረት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከ866 ሚሊዮን 7 መቶ ሺህ ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የጉራጌ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የዞኑ ገቢ የመሰብሰብ አቅም ለማሳደግ ህብረተሰቡ የሚጠይቃቸው የልማት ስራዎች ማፋጠን እንደሚገባ የወልቂጤ ከተማ ያነጋገርናቸው የንግዱ ማህበረሰብ ገለጹ፡፡

በጉራጌ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የልማት እቅድ ዝግጅት አፈፃፀም ክትትልና መረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ስዩም ቀድሩ እንደገለፁት በዞኑ ለሚገኙ 25 ሺህ 910 ግብር ከፋዮች ልዩ ልዩ ስልጠናዎች መስጠት ተችሏል፡፡

በዚህም አብዛኞቹ ግብር ከፋዮች ግብር እና ታክስ የመክፈል ግዴታቸው በአግባቡ እንዲወጡ አስችሏቸዋል ብለዋል።

የታክስ መሰረት በማስፋት ኢኮኖሚውን የሚያመነጨው ገቢ ለመሰብሰብ በግማሽ አመቱ 2 ሺህ 441 አዳዲስ ግብር ከፋዮች መመዝገብ እንደተቻለ አስረድተዋል።

በመሆኑም ባለፉት ስድስት ወራት ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤት 840 ሚሊዮን 450 ሺህ ብር ለመሰብሰብ ታቅዲ 866 ሚሊዮን 720 ሺህ 795 ብር መሰብሰብ እንደተቻለ አቶ ስዩም አስረድተዋል፡፡

ህብረተሰቡ በመሰረተ ልማት ስራዎች ተጠቃሚ ለማድረግ ገቢ የመሰብሰብ አቅም መጎልበት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው የገለፁት አቶ ስዩም ህብረተሰቡ ለሚያገኘው አገልግሎት የከፈለበትን ደረሰኝ የመጠየቅ ባህሉ ሊጎለብት ይገባል፡፡

የግብር እና ታክስ ህግ አክብረው በማይሰሩ 248 ግብር ከፋዮች ላይ መረጃ በማሰባሰብ 81 ግብር ከፋዮች መተማመኛ የፈረሙ ሲሆን 64 ግብር ከፋዮች ማስጠንቀቂያ እንዲሁም 11 ግብር ከፋዮች እያንዳንዳቸው 50 ሺህ ብር ተቀጥተዋል ብለዋል።

በወልቂጤ ከተማ የገብሬ ማሞ ሆቴል ስራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ ሙሉ እና የሳሬም ሆቴል ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት ምህረት ደገሙ እንዲሁም ኑርበገን መልካ የኬርቲና ሆቴል ስራ አስኪያጅ በጋራ በሰጡት አስተያየት የዞኑ ገቢዎች ባለስልጣን በወጪ አያያዝ፣ በደረሰኝ አቆራረጥ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እያደረገ ያለው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡

ግብር ከፋዮቹ በተደረገላቸው ድጋፍ ግብር እና ታክስን በወቅቱ ለመክፈል እንዳስቻላቸው ገልፀዋል፡፡

እንደግብር ከፋዮቹ ገለፃ የህብረተሰቡ ኑሮ ለማሻሻልና የከተሞች እድገት ለማፋጠን ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ግብርና ታክስን በወቅቱ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡

አያይዘውም ግብር ከፋዮቹ የዞኑ ገቢ የመሰብሰብ አቅም ለማሳደግ ህብረተሰቡ የሚጠይቃቸው የልማት ስራዎች ማፋጠን ይገባ ። ለዚህ ደግሞ መንግስት ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *