መስከረም 03/2015
በ 2015 በጀት ዓመት 9 መቶ 37 ለሚሆኑ ወጣቶችና ጎልማሶች የስራ እድል ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በ 2014 በጀት ዓመት በተለያዩ የስራ ዘርፎች 9 መቶ 61 ለሚሆኑ ስራ አጥ ዜጎች የስራ እድል መፍጥር መቻሉም ተገልጿል ።
የእምድብር ከተማ አስተዳደር ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉ ለማ እንደገለጹት ቀድምት ባሉ ዓመታት የተደራጁ ማህበራትን በማጠናከር ለሌሎች ወጣቶች ጊዜያዊ የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ ማድረጋቸውን አብራርተዋል።
በማኑፋክቸሪንግና ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ 9 መቶ 61 ለሚሆኑ ስራ አጥ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ የገለጹት ወይዘሮ ሙሉ ለማ አዋጪነት ያላቸውን ስራዎች በመለየትና በፈለጉት የስራ መስክ በመሰማራታቸው ዉጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከ 2 ሚሊዮን 4 መቶ ሺህ ብር በላይ ከዚህ በፊት የ ያልተመለሰ ብድር መኖሩን የገለጹት ኃላፊዋ ከዚህ ውስጥ ከ 9 መቶ 81 ሺህ ብር በላይ ማስመለስ መቻሉን ገልጸዋል።
በ 2015 በጀት ዓመት ለ 1 ሺህ 4 መቶ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ዕቅድ እንደተያዘ ገልጸው እስካሁን 9 መቶ 37 ወጣቶችና ጎልማሶች በመለየት የስራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ወይዘሮ ሙሉ ለማ ተናግረዋል።
ከዞንና ከከተማ አስተዳደር 6 ሚሊዮን 5 መቶ ሺህ ብር በዘንድሮው አመት ለስራ ፈጠራ ለሚሰማሩ ወጣቶች እንደሚሰራጭ ጠቁሟል።
በእምድብር ከተማ 01 ቀበሌ ስራ ከተፈጠረላቸው መካከል አቶ ሳህሌ በርታ እንደገለጹት ከዚህ በፊት በሚሰሩት ስራ ቤተሰብ ማስተዳደር እንደተሳናቸው ገልጸዋል ።
ከተማ አስተዳደሩ በወተት ላም እርባታ በማህበር አደራጅቷቸው አሁን ጥሩ ደርጃ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።