የመንግስት ሀብትና ንብረት እንዳይባክን ሲቪል ሰርቫንቱ ከመቼዉም ጊዜ በላይ በመታገልና በሀገሪቱ ልማትና እድገት ላይ የሚፈለገዉን ዉጤት ማምጣት ይገባል።
በአለም አቀፍ ለ18ኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ለ17ኛ ጊዜ በክልሉ ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ “በስነ_ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ ” በሚል መሪ ቃል አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን የዞኑ አጠቃላይ ሰራተኞችና አመራሮች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል።
በእለቱም የተገኙት የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ክፍሌ ለማ እንዳሉት በሀገሪቱ እድገትና ለዉጥ እንዲመጣ ለማድረግ የመንግስት ሰራተኞች ከመቼዉም ጊዜ በላይ የጸረ ሙስና ትግሉ ላይ በትኩረት ሊሰሩበት ይገባል ብለዋል።
አሁን ላይ ሀገራችን ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር አብዛኛው ሀብት በጦርነት ምክንያት እየባከነ እንደሆነም ያስረዱት አቶ ክፍሌ በዚህ ምክንያት ልማት ላይ ያልዋለውን ሀብት በቁጠባ መጠቀም እንደሚገባም አሳስበዋል።
ሙስና የገንዘብ ስርቆት ብቻ ሳይሆን ከተመደብንበት የስራ ሀላፊነት አንፃር በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል አለመቻልም አክለዉ ገልጸዋል።
የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት የስነ ምግባር ኦፊሰር አቶ ጀማል አህመድ በበኩላቸዉ
የፀረ ሙስና ቀን በአለም አቀፍ ለ18ኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ለ17ኛ ጊዜ በክልሉ ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ በዞናችን ደግሞ ለ10ኛ ጊዜ”በስነ_ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና የጸዳች ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ሲከበር አላማው በሙስና ላይ ህዝባዊ ንቅናቄ እና ትግል ለመፍጠር ታስቦ እንደሆነም አመላክተዋል።
ሙስና ስልታዊና ውስብስብ በመሆኑ ለሀገሩ የሚቆረቆር ትውልድ ለመፍጠር ባለድርሻ አካለት ርብርብ ማድረግ አለባቸው ሲሉ የገለፁት አቶ ጀማል የሚያስከትላቸው ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውሶቹ ከፍተኛ በመሆኑ ከምንጩ ለማድረቅ በቅንጅት መሰራት እንዳለበትም አሳስበዋል።
በእለቱ የተገኙ አንዳንድ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ባለመኖሩ ምክንያት ውስን አካላት ላይ የሚታየው የስነ ምግባር ችግር ሳይቀረፍ ቆይቷል ብለዉ ይህን ችግር ከምንጩ ለማድረቅ
ሁሉም ሰዉ ትግል ማድረግ እንዳለበትም አስታዉቀዋል።
በእያንዳንዱን ተቋም መነሻ አድርጎ ያለውን የስነምግባር ብልሹ አሰራር ጥናት ተደርጎ ቢቀርብ የሚል አስተያየታቸዉ ሰጥተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።
አካባቢህን ጠብቅ!
- ወደ ግንባር ዝመት!
- መከላከያን ደግፍ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx