በጤናውን ዘርፍ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ የህዝብ ውይይት መድረኮች በማዘጋጀት ህዝቡ አጋዥ ማድረግ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያዉ የ2013 ዕቅድ አፈጻጸምና የ2014 የአንደኛ ሩብ አመት አፈጻጸም ግምገማ ከወረዳና ከከተማ አስተዳደሮች የጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሄዷል፡፡

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሹ አማን በመድረኩ ተገኝተዉ እንዳሉት የጤና ሴክተር የልማት እቅድን ለማሳካት ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር ስኬታማ ስራዎች መስራት እንደሚገባም አስረድተዋል።

በዞኑ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት በማሻሻልና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ በበጀት አመቱ በስፋት መሰራት እንደሚገባም አስረድተዋል።

የወባ በሽታ ለማጥፋት እየተሞከረ ባለበት በአሁኑ ወቅት እንደ አዲስ በዞኑ በተለያዩ አከባቢዎች በስፋት እየተዛመተ መሆኑም አብራርተዉ ይህንንም ለመከላከል የጤና ተቋማቶች አበክረዉ ሊሰሩበት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በጤናውን ዘርፍ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ የህዝብ የውይይት መድረኮች በማዘጋጀት ህዝቡ አጋዥ በማድረግ የጤናዉን ዘርፍ ማጠናከር እንደሚገባም ተመላክቷል።

ነፍሰጡር እናቶች የወሊድ ክትትል በጤና ተቋማት አለማድረግ የሚያስከትለውን የህጻናት እና የእናቶች ሞት በአግባቡ አለማስረዳት እና መረጃዎች በአግባቡ አደራጅቶ የመያዝ ችግሮች እንዳለም ገልጸው ይህንን ችግር ለመቅረፍ በቀጣይ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የአፈጻጸም ድክመት ያለባቸው ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ድክመቶቻቸውን በማረምና የሰው ሀይል የህክምና ቁሳቁስ በማሟላት ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ለህብረተሰቡ መስጠት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

የጤና ጣቢያዎችና የሆስፒታሎች ትስስር በማጠናከር የልምድ ልዉዉጥ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ጥራት በማሻሻልና በማዘመን በቀጣይ አጽእኖት ተሰጥቶት እንደሚሰራም አብራርተዋል።

የህብረተስቡ የጤና መድህን አገልግሎት አሰጣጥ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ጤና ተቋማቶች ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸዉም አመላክተዋል።

ያነጋገርናቸው የመድረጉ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በጤናዉ ዘርፍ የሚፈለገዉ ዉጤት እንዲመጣ ያለባቸውን ክፍተት በአግባቡ በማረምና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ከአቅም በላይ የሆኑ ጉዳዮችን ከዞኑ ጤና መምሪያ እንዲሁም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር የተቀዛቀዘዉን የጤናዉን ዘርፍ በማነቃነቅ የሚፈለገዉን ዉጤት ማምጣት እንደሚገባም አስረድተዋል።

በመድረኩም ከሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳድሮች የተዉጣጡ የጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላቶች ተሳትፈዋል ሲግን ል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግሰት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው፡

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *