በጎነት ለጤናችን” በሚል መሪ ቃል በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ከ30 ዩኒት በላይ ደም መለገሳቸውን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አስታወቀ።

ነሐሴ 21/2014 ዓ.ም

“በጎነት ለጤናችን” በሚል መሪ ቃል በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ከ30 ዩኒት በላይ ደም መለገሳቸውን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በወረዳው የ 2014 የክረምት በጎ ስራ ከ13 ሺህ 300 በላይ ወጣቶች በተመረጡ 16 የስምሪት መስኮች ላይ ተሰማርተው መጠነ – ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ከነዚሁ የበጎነት ማሳያ የአብሮነት እና ወንድማማችነት እሴቶች መካከል ደግሞ በወጣቶችና በህብረተሰቡ ዘንድ ተግባራዊ እየሆነ ያለው “የደም ልገሳ” አንዱና ዋነኛው ነው።

በወሊድ ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶች ሞት ለመከላከል ፣ የጤና እክል ያጋጠማቸው ወገኖች በደም እጦት ምክንያት ክቡር የሆነውንና መተኪያ የማይገኝለትን የህይወት ህልፈትን አስቀድሞ ለመከላከል አሊያም ደግሞ የሞት ምጣኔውን ለመቀነስ በጎ ፈቃደኞች የሚለግሱት ደም የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው።

ይህንንም መሰረት በማድረግ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር 80 ዩኒት ደም በክረምቱ ወራት ለማሰባሰብ ታቅዶ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን እስካሁን ባለው ሂደት ብቻ ከተለያዩ የህብረተሰብ በክፍሎች 31 ዩኒት ደም በመሰብሰብ በወሊድ ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶች ሞት እና በደም እጦት ምክንያት በዜጎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ህልፈት ለማስወገድ ብርቱ ጥረት ማድረግ መቻሉን ከወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት የደረሰን መረጃ ያመላክታል ሲል የዘገው የገ/ጉ/ወ/ወ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነው።
“ሰው ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው”

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *