በግብርና ዘርፍ ኢንቨስትመንት ከተሰማሩ 3 መቶ 71 ፕሮጀክቶች 5 ሺህ 12 ሔክታር መሬት መልማቱን የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንት መምሪያ አስታወቀ።

ነሐሴ 10/2014 ዓ.ም

በግብርና ዘርፍ ኢንቨስትመንት ከተሰማሩ 3 መቶ 71 ፕሮጀክቶች 5 ሺህ 12 ሔክታር መሬት መልማቱን የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንት መምሪያ አስታወቀ።

በኢንቨስትመንት መሬት ተረክበው ወደ ተግባር ባልገቡ 7 የኢንቨስትመት ፕሮጀክቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል።

የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመን መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘነበ ደበላ እንደገለፁት ባለሀብቶች በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ ፈቃድ አውጥው ወደስራ በመሰማራታቸው ለ5 ሺህ በላይ ቋሚና ከ15 ሺህ በላይ ጊዜያዊ የስራ እድል መፈጠሩን ገልፀዋል።

በዞኑ በኢንቨስትመንት ከተሰማሩ 3 መቶ 71 ፕሮጀክቶች 7 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ማስመዝገብ መቻሉን ጠቅሰው ከዚህም ውስጥ 5 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በዞኑ ላይ ፈሰስ መደረጉን አብራርተዋል።

እንደ አቶ ዘነበ ገለፃ ለሶስቱም የኢንቨስትመንት ዘርፎች ከተላለፈው 7 ሺህ 2 መቶ 47 ሔክታር መሬት ውስጥ 5 ሺህ 12 ሔክታር መሬት መልማት ችሏል።

ለባለሀብቶች ተላልፎ ያለሙ 2 መቶ 45 ሔክታር መሬት ወደ መሬት ባንክ በማስገባት 27 የሚሆኑ ባለሐብቶች ላይ በአሰራሩ መሠረት እርምጃ መወሰዱ አቶ ዘነበ አስረድተዋል።

በዞኑ ውስጥ በኢንቨስትመንት ከተሰማሩ ባለሀብቶች መካከል የግሎባል ምግብ ማቀነባበሪያ ባለቤት አቶ አብድልወኪል ግራኝ በ2008 አመተ ምህረት ላይ ወደተግባር በመግባት ለ27 ቋሚና ለ17 ያህል ጊዜያዊ ሰራተኞች የስራ እድል ፈጥረዋል።

እንደ አቶ አብድልወኪል ገለፃ በቀን አስከ 4 መቶ 80 ኩንታል ዱቄት ማምረት እንደሚችልና ለዚህም ውጤት በኩታ ገጠም የተመረተው የበጋ መስኖ ስንዴ የግብአት እጥረት መቅረፉና የተቋሙ የማምረት አቅሙንም ማሳደግ መቻሉን አስረድተዋል።

ከኢንቨስትመንቱ ጎን ለጎን በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ላይ ትኩረቱን በማድረግ የውሀ ጉድጓድ በማስቆፈር ለአካባቢው ሰው የውሀ ችግርን መቅረፍ መቻሉንና የአቅም ችግር ላለባቸው ዱቄት በፋብሪካ ዋጋ እያቀረበ ይገኛል ብለዋል።

ፋብሪካው የወቅቱን የኑሮ ውድነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በወልቂጤ ከተማ በተቋቋመው የቅዳሜ ገበያ ምርቱን እያቀረበ ነው ።

ከፋብሪካው ስራ ጎን ለጎን በሆቴል ስራላይ ለመሰማራት ከመንግስት መሬት ተረክቦ ወደተግባር መግባቱን አስረድቷል።

በረጃ ምጭነት ገፃችንን ስለምትከታተሉ እናመሰግናለን!
እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *