በግማሽ አመቱ 36 ሺህ በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በዞኑ መንግስት 13 ሚሊየን ብር ድጋፍ የማጤመ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ የጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ አስታወቀ።

ማህበራዊ ፍትህ፣ፍትሃዊ የሆነ የስራ ስምሪትና አገልግሎት ለማስፋፋት በትኩረት እየሰራ መሆኑ መምሪያ አስታውቋል።

መምሪያዉ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊዎች፣ባለሙያተኞችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የ2014 አመተ ምህረት የግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በወልቂጤ ከተማ አካሄዷል።

የጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ አመተሩፍ ሁሴን በመድረኩ እንደገለፁት እንደ ተቋም ማህበራዊ ፍትህን ለማረጋገጥ፣ፍትሃዊ የሆነ የስራ ስምሪትና አገልግሎት የተስፋፋበት አካባቢ ለመፍጠር አላማ አንግበዉ እየተሰራ ይገ ኛል።

ማህበራዊ ፍትህን ለማረጋገጥ፣ፍትሃዊ የሆነ የስራ ስምሪትና አገልግሎት የተስፋፋበት አካባቢ እና ሰላማዊ የሆነ ኢንዱስትሪ ለመፍጠር አመራሩና ባለሙያው በእዉቀት መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት በተቋሙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማስተባበር ለችግር የተጋለጡ አካላቶች በመለየት ድጋፍ ለማድረግ 5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ለተጋላጭ ወገኖች ሀብት ለማሰባሰብ ታቅዶ በዚህም በተደረገዉ ከፍተኛ ጥረት 5 ሚሊየን 4 መቶ 56 ሺህ 889 ብር በአይነትና በገንዘብ ሀብት የማሰባሰብ ስራም መሰራቱም ገልፀዋል።

በመጀመሪያው ግማሽ አመት 36 ሺህ የደሃ ደሃ ወይም በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት እንደ ዞን በመንግስት 13 ሚሊየን ብር ድጋፍ የማጤመ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉም ተናግረዋል።

የአካል ጉዳተኞች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አካላዊ ተሀድሶ አገልግሎትና የዊልቸር ድጋፍ እንዲያገኙ የማድረግ ስራ በመስራት በመጀመሪያዉ ግማሽ አመት ለ54 አካል ጉዳተኞች ዊልቸር እንዲያገኙ የማድረግ ስራ መስራቱም አስረድተዋል።

የእግር መቆልመም የገጠማቸዉ ህጻናትም ከቲሻየር ኢትዮጵያ ጋር በመነጋገር አካላቸዉ እንዲጠገን መደረጉም ያብራሩት ሀላፊዋ የዞኑ አስተዳደር ለአካል ጉዳተኞች የዊልቸር ተጠቃሚ እንዲሆኑ 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉም አስታዉቀዋል።

በቀጣይ ግማሽ አመት የተቋሙ ዉጤታማነት በዘላቂነት ለማስቀጠል የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ጥረት የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸው እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በመድረኩ የተገኙ አንዳንድ ባለድርሻ አካላቶች በሰጡት አስተያየት በቀጣይ የመረጃ አያያዝ ስርአት በማዘመንና የድጋፍና ክትትል ስራዉ አጠናክሮ በማስቀጠል በሴክተሩ የሚጠበቀዉን ዉጤት ማምጣት ይገባል።

ዜጎች ላላስፈላጊ እንግልትና ስቃይ እንዳይዳረጉ ህገወጥ የሰዎች ዝዉዉር ለማስቆም ከመቼዉም ጊዜ በላይ አጽእኖት ሰጥተዉ እንደሚሰሩም አብራርተዋል።

ለአረጋዉያንና ለአካል ጉዳተኞች ትኩረት በመስጠት ተጠቃሚነታቸዉ ማረጋገጥ እንደሚገባና በተለያዩ አካባቢዎች አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት ተቋማት ግንባታዎች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አለመሆናቸዉ ገልፀው በቀጣይ ችግሩ ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

ለተለያዩ ችግር የተጋለጡ ወገኖች የማጤመ አግልግሎትና በሌሎቾም ዘርፎች ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ የተጀመረዉን በጎ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላክተዋል ።

በመድረኩም የተቋሙ የቀጣይ 6 ወራት የትኩረት አቅጣጫዎችና የማስፈፀሚያ ስልቶች መግባባት ተፈጥረዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *