በግል ክሊኒኮችና መደብሮች በህገወጥ መንገድ የገቡ መድሀኒቶች እና በዞኑ ጤና መምሪያ ለረጅም ጊዜ የቆዩ የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶች ማስወገዱን የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ።

የተወገዱ መድሀኒቶች ዋጋ 35 ሺህ 161 ብር እንደሆነም ተገልጿል ።

ሁሉም የመድሀኒት አይነቶች በሁሉም መድሃኒት መደብሮች እንዲገኙ አይፈቀድም። መደብሮቹ በሚሰጣቸው ደረጃ እና ባላቸው የሰው ሀይል አቅም ይወሰናል። ይሁን እንጂ በጉራጌ ዞን በተለያዩ ከተሞች ከደረጃቸው በላይ ማለትም በትልልቅ ሆስፒታሎች ደረጃ ብቻ መገኘት የሚገባቸው መድሀኒቶች ጭምር ስለሚሸጡ በድርጅቶቹ ላይ እርምጃ እየተወሰደባቸው ይገኛል።

በመምሪያው የጤናና ጤና ነክ ግብዓት ጥራት ቁጥጥር አስተባባሪ አቶ ደርቡ ደገሙ መድኃኒቶቹ የተወረሱት ከግል መድኃኒት መደብሮችና ክሊኒኮች እንደሆኑ ገልጸዋል።

መድኃኒቶቹ የተወረሱት በግል መድኃኒት መደብሮችና ልሊኒኮች ላይ መገኘት የሌለባቸውና ከተቋማቱ ደረጃቸ በላይ የሆኑ መድኃኒቶች ሲሸጡ በመገኘታቸው እንደሆነም አስተባባሪው ተናግረዋል።

አክለውም አቶ ደርቡ በዞኑ ጤና መምሪያ የአገልግሎት ጊዜ አልፎባቸው የተከማቹ መድኃኒቶች ጭምር ተወግደዋል ብለዋል።

መድሀኒቶቹ ደግሞ በተራድኦ ድርጅቶች የቀረቡ ሲሆን መድሀኒቶቹ በቀረቡበት ወቅት የአገልግሎት ጊዜያቸው ማብቂያ የተቃረቡ በመሆናቸው ለጤና ተቋማት ሳይሰራጩ የቆዩ እንደሆኑ ነው አስተባባሪው የገለጹት።

በአሁን ወቅት ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት አቶ ደርቡ ለዚህ ደግሞ ደረጃቸው ያልጠበቁና የተበላሹ በመሆናቸው ከሚሰጡት ፈውስ የሚያስከትሉት የጤና ቀውስ ይበልጣል ብለዋል።

ደረሰኝ የሌላቸው፣ በኮንትሮባንድ የገቡ ፣ምንጫቸው ያልታወቁና የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶች በተጠቃሚዎች ጤና ላይ የሚያሳድሩት የጎንዮሽ ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ መምሪያው በመድሀኒት መደብሮችና ክሊኒኮች ላይ የሚያደርገው ቁጥጥርና ክትትል ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል ።

መድሃኒቶቹ ከጸጥታ፣ ከፋይናንስ፣ ከጤና መምሪያ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ ኮሚቴዎች በተገኙበት እንዲወገዱ ተደርጓል።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *