በጉራጌ ዞን 7 ሺህ 7 መቶ 45 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ በነገዉ እለት ለፈተና ይቀመጣሉ።

በጉራጌ ዞን 7 ሺህ 7 መቶ 45 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ በነገዉ እለት ለፈተና ይቀመጣሉ።

የብሔራዊ ፈተናዉን አስመልክዉ መረጃ የሰጡን የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ እንዳሉት በመደበኛና በግል ወንድ 4,361 እንዲሁም ሴት 3,384 በድምሩ 7,745 ተፈታኝ ተማሪዎች በነገዉ እለት በሚሰጠዉ የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የተፈታኝ ተማሪዎች አድሚሽኝ ካርድ ከሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በመረከብ በ21 ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ተፈታኝ ተማሪዎች በወቅቱ የማሰራጨት ስራ ተሰርቷል፡፡

በዞኑ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ መስተዳደሮች ፈተናው በ58 የመፈተኛ ጣቢያዎች ላይ የሚሰጥ እንደሆነም ያስረዱት አቶ አስከብር በነገዉ እለት ለሚጀመረው ሀገር አቀፍ ፈተና በቂ የጸጥታ ሀይሎች በሁሉም አካባቢዎች ፈተናዉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ተሰማርተዋል ብለዋል።

የኩረጃን አስከፊነት በሚመለከት በፈተና ወቅት የተከለከሉ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ይዘዉ እንዳይገቡ የግንዛቤ ስራ በዞኑ የትምህርት መምርያ ባለሞያዎች ጨምሮ በሁሉም የድጋፍና ክትትል ስራ በሚፈፅሙ አካላት እየተሰራ ሲሆን በፈተና መግቢያ እና በፈተና ወቅትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው ብለዋል።

ሌሎች ፈተናዉ ያለምንም የፈተና ደምብ ጥሰት እንዲከናወን ከፈተና ስርጭት፣ አሰጣጥና የመልስ ወረቀት ርክክብ ድረስ ያለው ስራ በእቅድ ተይዞ እየተከናወነ ይገኛል።

ለፈተና አስፈፃሚዎችና ተፈታኞች ከሚጠበቅባቸው ተግባራትና ሀላፊነት አንፃር መመሪያን መሰረት ያደረገ ኦረንቴሽን በየደረጃው የተሰጠ መሆኑንና የመፈተኛ ክፍሎች ከተማሪ ቁጥር አንፃር እንዲደራጁ ተደርጎአል ብለዋል።

የፈተና ርክብክብና ስርጭት ከትምህርት ሚኒስቴር እስከ ወረዳና ከተማ መስተዳደር ፖሊስ ጣቢያ በማድረስ አስተማማኝ ጥበቃ እየተደረገለት እንደሆነም አብራርተዋል።

ለዞንና ለወረዳ የፈተና አስፈፃሚ ኮማንድ ፖስት እና ለሌሎች ባለድርሻ ከካላት በዞኑ ማእከል በመጥራት ኦረንቴሽን የተሰጠ ሲሆን ፈተናው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትላቸው መጠናከር እንዳለበት አሳውቀዋል፡፡

የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች በሁለቱ ማእከል/በቡታጅራና በወልቂጤ ማእከል/ በመጥራት ከማእከል አስተባባሪዎች ጋር በመሆን ኦረንቴሽን በመስጠት ስምሪት ተሠጥቷል ሲሉም ገልፀዋል።

በመጨረሻም ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናው እንዲወስዱ እና ከተዛቡ መረጃዎች ራሳቸው ሊከላከሉ ይገባል ብለው ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅና ተማሪዎች ተረጋግተው እንዲፈተኑ መምህራን፣ወላጆች፣ወጣቶችና ሁሉም ባለድርሻ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ፡፡

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *