በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ ወንዝሬና ጎረት ቀበሌዎች ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻ መሆናቸውን ተገለጸ።

በዞኑ ህብረተሰቡ የተሻሻሉ መጸዳጃ ቤቶች የመጠቀም ባህሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ እያደገ በመምጣቱ “ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው “ጽዱ ኢትዮጵያን እንፍጠር” ሀገራዊ ንቅናቄ ቀድሞ ለማሳካት እንደተቻለ የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ በፕሮግራሙ ላይ እንዳሉት የጉራጌ ማህበረሰብ ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻ ለማድረግ በተሰራው ስራ ግንዛቤ ፈጥሮ የተሻሻሉ መጸዳጃ ቤቶ እየተጠቀመ ያለበት መንገድ አበረታች ነው።

የሰው ልጅ ክብሩን ጠብቆ ንጽህናውን በተጠበቀ መጸዳጃ ቤት ሊጠቀም ይገባል። ይህም በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ የታየው ምርጥ ተሞክሮ በክልሉ በሁሉም አካባቢ ሊሰፋ እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ በፕሮግራሙ ላይ እንዳሉት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ያስጀመሩት ጽዱ ኢትዮጵያ እንፍጠር ንቅናቄ ዞኑ ቀደም ብሎ “ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” በሚል መሪ ሀሳብ ህብረተሰቡ የአካባቢውንና የግል ንጽህና በጥሩ ሁኔታ እየጠበቀ ይገኛል።

በዞኑ ጌታ ወረዳ ወንዝሬና ጎረት ቀበሌዎች የተሻሻሉ መጸዳጃ ቤቶች ተጠቅመው አካባቢዎቹ ከአይነ-ምድር ነፃ መሆናቸውን በማረጋገጥ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በይፋ መመረቃቸውን ለተግባሩ መሳካት ማሳያ መሆኑን አቶ አየለ ገልጸዋል፡፡

ንጽህናው የሚጠብቅ ሰው ከሚያገኘው ማህበራዊና ኢኮሚያዊ ፋይዳው በተጨማሪ በማህበረሰቡም ዘንድ ከበሬታን እንደሚያገኝ የገለጹት አቶ አየለ ይህንንም ይበልጥ ውጤታ ለማድረግ በወረዳው አብዛኛው ማህበረሰብ የተሻሻሉ መጸዳጃ ቤቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ በትኩረት ሊሰራ ይገባል፡፡

የጌታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በህሩ ኸይረዲን በበኩላቸው በወረዳው ህብረተሰቡ የግልና የአካባቢው ንጽና እንዲጠብቅ በማድረግ ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋ ለመፍጠር በትኩረት መሰራቱን ገልጸዋል።

የወረዳው ህብረተሰብ በማሳተፍ በተሰራው ስራ ዛሬ ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻ መሆናቸውን ተረጋግጦ እውቅና የተሰጣቸው የወንዝሬና ጎረት ቀበሌዎች የዚህ ማሳያ መሆናቸውን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

በወረዳው የተሻሻሉ የመጸዳጃ ቤት ተጠቃሚዎች የመስክ ምልከታ ሲካሄድ እንዳሉት የግልና የአካባቢ ንጽና መጠበቃቸው ከተላላፊ በሽታ እራሳቸው በመጠበቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ አድርጎዋቸዋል።

ዛሬ በጌታ ወረዳ ወንዝሬና ጎረት ቀበሌዎች ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻ መሆናቸውን በማረጋገጥ የእውቅና ስነ-ስርዓት የክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ እና ሌሎች ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *