በጉራጌ ዞን ገ/ጉ/ወ ወረዳ የንፁህ መጠጥ ውሀ እጥረትን ለመቅረፍ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ።

02/01/2015 ዓ.ም

በጉራጌ ዞን ገ/ጉ/ወ ወረዳ የንፁህ መጠጥ ውሀ እጥረትን ለመቅረፍ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ።

የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንዳሉት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለመሃል አምባ ከተማ እና የአካባቢው የህብረተሰብ ክፍሎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ በዛሬው እለት ከባድ ማሽነሪዎች እና ተጨማሪ ግብአቶችን ወደ ወረዳው ማስገባቱን በማስመልከት ለመላው የወረዳችን ነዋሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለመሃል አምባ ከተማ እና ለአካባቢው የህብረተሰብ ክፍሎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ በዛሬው እለት ለፕሮጀክቱ ቁፋሮ እና ግንባታ ስራ የሚውል የተለያዩ ከባድ ማሽነሪዎች እና ተጨማሪ ግብአቶችን ወደ ወረዳው አስገብቷል።

የጥልቅ ጉድጓድ የንፁህ መጠጥ ውሃ ጥናትና ዲዛይን ስራው በወረዳው ጥላሞ ቀበሌ ሴጦ ኮሎ ጎጥ ላይ ተሰርቷል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሙሉ የግንባታ ወጪውን በመሸፈን የጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራውን የጀመረ ሲሆን ሙሉ ማሽነሪዎችንና ግብአቶቹንም በስፍራው አስገብቷል ሲል የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *