በወረዳው ከተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ህዝባዊ አደረጃጀቶች መሰረታዊ የአከባቢ ደህንነት ጥበቃ እና የፀጥታ ስራን ለማሳለጥ ለ5 ተከታታይ ቀናት ሲሰለጠኑ የነበሩ ሠልጣኞች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል።
በምርቃቱ ስነ ስርአቱ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የጉራጌ ዞን ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አርሽያ አህመድ እንዳሉት ሀገራችን ኢትዮጵያ ጀግና እና ቆራጥ ልጆቿ እያሏት በፍፁም አትፈርስም ከውስጥና ከውጭ የተደቀነብንን ሴራ አክሽፍን ድል እያደረግን መሆኑን አስታውቀዋል።
በህዝባዊ አደረጃጀት በመቀናጀት ሁሉም ህብረተሰብ ክፍል በየአካባቢው ዘብ እንዲሆኑና ከሰርጎ ገቦችና ከተላላኪዎች አከባቢዉን እየጠበቁ ለመከላከያ ሠራዊታችን ያለንን ደጀንነት ማስመሰከር እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን አፈ ጉባኤዋ አሳስበዋል፡፡
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙራድ ረሻድ እንደተናገሩት እንደሚታወቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት የውስጥና የዉጭ ባንዳዎች ዘመናዊ ባርነትን ለማስፋፋት አይችሉምና ሀገራችን የገጠማትን ችግርን ተቋቁማ ቀና አድርጋ የምትነሳበት ጊዜ ደርሷል ብለዋል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ ለቅኝ ግዛት ያልተንበረከከች ሉዓላዊት እና ክብሯን አስጠብቃ ያኖረች እንዲሁም የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት መሆኗን የዉስጥም የዉጭም ኃይሎች ጠንቅቀው ያውቋታልም ብለዋል።
ሰልጠኞቹ የህዋሃትን እኩይ ሴራ አጀንዳ ተሸክሞ የሚንቀሳቀሱ ሰርጎ ገቦች ሊኖሩ ሲለምችሉ የአከባቢያችንን ሰላም እና ፀጥታ ለማስጠበቅ የወሰዳችሁትን ስልጠና ተግባራዊ እንደምታደርጉ እምነቴ የፀና ነው ብለዋል።
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ አ/ሂም ርዳ በበኩላቸው ጠንካራ ህዝባዊ ሰራዊት በሁሉም አካባቢዎች በማደራጀት የአካባቢዉንና የወረዳውን ብሎም የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡
በዛሬው እለት 273 አባላት ስልጠና መወሠዳቸውን በመግለጽ 30 ጓድ አደረጃጀት፣ 9 መቶ አደረጃጀት እና በ3 ሻምበል በማደራጀት መሠረታዊ የውትድርና ሳይንስ ለ5 ተከታታይ ቀናት ሲሠለጠኑ እንደነበር ገልጸዋል።
ተመራቂ ሰልጠኞች በስጡት አሥተያየት የአካባቢያቸውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ዝግጁ መናቸውንም ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ለሠልጠኞች የምስክር ሠርተፍኬት በመስጠት የምርቃ ስነ ስርዓቱ ተጠናቋል ሲል መረጃው ያደረሰን የወረዳው የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።
- አካባቢህን ጠብቅ!
- ወደ ግንባር ዝመት!
- መከላከያን ደግፍ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx