በጉራጌ ዞን ደቡብ ሶዶ ወረዳ 1 መቶ 65 ሄክታር መሬት በላይ የማልማት አቅም ያለዉ የሲቢስቶ አነስተኛ የመስኖ ግድብ ግንባታ ስራ የቦታ ርክክብ ተደረገ።

በርክክቡ ወቅት የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ከፍተኛ የምህንድስና ባለሙያዎች ፡የዞን ዉሃና ማዕድን ባለሙያ ፡የወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊና የተፈጥሮ ኃብት ልማት ዘርፍ አስተባባሪ የደቡብ ሶዶ ወረዳ ዉሃ ማዕድን ፅ/ቤት የዉሃ ምንድስና ባለሙያ አቡሽ ታሪኩ ዉሃነክና ጠቅላላ ዉሃ ስራዎች ተቋራጭ ጋር የቦታ ርክክብ አድርገዋል።

የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ አነስተኛ መስኖ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ የዉሃ ሃብት መሃንዲስ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሞልቶት ኤልያስ የመሶኖ ግድብ ግንባታዉ 1 መቶ 65 ሄክታር መሬት የማልማት አቅም ያለዉ እንደሆ ገልፀው።

የግንባታው አጠቃላይ በጀት 32 ሚሊየን ብር የሚወስድ እንደሆነና ሙሉ ወጭዉን የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ የሚሸፈን ሲሆን ስራዉ በቅርብ ቀናት እንደሚጀምር እና ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ግንባታዉ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚሰጥ ታሳቢ በማድረግ ከተቋራጩ ጋር ስምምነት እንደተደረሰ አመላክተዋል ሲል የዘገበው የደቡብ ሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *