በጉራጌ ዞን የ12ኛ ክፍል የመጀመርያው ዙር ተፈታኞች ፈተናቸውን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማጠናቀቃቸውን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ገለፀ።

ጥቅምት 2/2015ዓ.ም

በጉራጌ ዞን የ12ኛ ክፍል የመጀመርያው ዙር ተፈታኞች ፈተናቸውን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማጠናቀቃቸውን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ገለፀ።

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ እንደገለፁት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት የሶሻል ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናቸውን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማጠናቀቃቸውን ገልፀው ተማሪዎቻቸውን ወደየ ቤተሰቦቻቸው ማድረስ መጀመራቸውን ገልፀዋል።

እንደ ሀላፊው ገለፃ የእምድብር፣አገናና ወልቂጤ ከተማ ነዋሪ ተማሪዎቻቸውን እንደሸኙ ገልፀው ቀሪ ተማሪዎቻቸውንም በነገው እለትም ወደየ አካባቢያቸው እንደሚያደርሱ ገልፀዋል።

አቶ እስከብር አያይዘውም የፈተና ስርዓቱ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን የበኩላቸውን ሚና ለተወጡ ተማሪዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን የቀጣይ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎችንም ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *