በጉራጌ ዞን የጤናማ እናቶች ወር “እናት ደህና ልጅም ጤና” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ እንደሚገኝ የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ፡፡

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ የእናቶች ህጻናት ጤናና ስርዓተ- ምግብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቸሩ አስፋው የጤናማ እናቶች ወር መከበርን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የጤናማ እናቶች ወር “እናት ደህና ልጅም ጤና” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዞኑ የጤናማ እናቶች ወር መከበሩ እናቶች በወሊድ ጊዜ በሚፈሳቸው ደም ምክንያት እንዳይሞቱ በጤና ተቋማት በሚገኙ የእናቶች ማረፊያ ላይ ሆነው አስፈላጊውን የጤና ክትትል እየተደረገላቸው በሰለጠነ ባለሙያ እገዛ እንዲወልዱ ለማድረግ የሚያስችሉ ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎችንና ሌሎች ድጋፎች ለማግኘት የሚረዳ የፓናል ውይይት ከሚመለከታቸው ባለድራሻ አካላት ጋር በመሆን በትምህርት ቤቶች፣ በቀበሌዎችና በሴቶች የህብረት ልማት ቡድን ደረጃ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመሆኑም በደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶች ሞት ለመቀነስ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አቶ ቸሩ ጥሪ አቅርበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *