በጉራጌ ዞን የግሉ ባለሀብት የኢንቨስትመንት ፍቃድ ወስደዉ ከ6 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ መዋለ ንዋይ በማፍሰስ ወደ ስራ የገቡ ባለሀብቶች መኖራቸዉም የጉራጌ ዞን አስተዳድር አስታወቀ።

የግሉ ኢንቨስትመንት ልማት ለማፋጠን የሀገራችን ብልጽግና እናረጋግጣን በሚል በዞኑ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች ፣ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎችና ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቡታጅራ ከተማ ፎረም ተካሄዷል።

የዞኑን ሁለንተናዊ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስና ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ይኖርባቸዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በፎረሙ ላየወ እንዳሉት የግሉ ባለሀብት የኢንቨስትመንት ፍቃድ ወስደዉ ከ6 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ መዋለ ንዋይ በማፍሰስ ወደ ስራ የገቡ ባለሀብቶች መኖራቸዉም ተናግረዋል።

የመንግስትና የግል ባለሀብቱ ጥምረት በመፍጠር በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገትና ልማት ትልቅ ለዉጥ ማምጣት ይቻላል ብለዋል።

በሀገር ደረጃ በዉጭ ምንዛሬ ግኝት ማዳን እንዲሁም ጥራት ያለዉ ምርጥ ዘር በማባዛትና በማቅረብ የአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ የዞኑ ባለሀብቶች ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሆነም አመላክተዋል።

በቅመማ ቅመም ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ በአበባ እርሻ ልማት ምርቶች እንዲሁም ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎች ምቹ ሲሆን በእነዚህ ዘርፎች የሚፈለገዉን ለዉጥ እንዳልመጣ አስታዉቀዉ ለዘርፉ እድገት የዞኑ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ እንደሆነም አብራርተዋል።

የደቡብ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀልገዩ ጀሌ በበኩላቸዉ የዞኑ የኢንቨስትመንት ፍሰት በተለይም በማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ በፍጥነት እያደገ እንደመጣም አመላክተዋል።

በዞኑ ባለፉት የለዉጥ አመታት ብቻ ከ196 በላይ ፕሮጀክቶች ያቀረቡ ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሰማሩ በክልሉ መንግስት መፈቀዱ በዞኑ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ፍሰት እያደገ መሆኑም ማሳያ ነዉ ብለዋል።

መሬት ወስደዉ የሚያለሙትን በማበረታታት መሬት ወስደዉ ወደ ልማት ያልገቡ የግሉ ባለሀብት እርምጃ ሊወሰድባቸዉ ይገባል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንትመት ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ዘነበ ደበላ እንዳሉት የግሉ ባለሀብቱእንዲያለሙ ተገቢውን ድጋፍና ከትትል ተደርጎላቸው መሬት ብቻ አጥረዉ ያስቀመጡ ባለሀብቶች ላይ ከሚመለከተዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ እንደሚወሰድም ተናግረዋል።

በቀጣይ ከተለያዩ የአለም ሀገራት የሚገኙ አዳዲስ ዲያስፎፓራዎችና ባለሀብቶች መጥተዉ እንዲያለሙ ፎረሙ እድል የሚፈጥር እንደሆነም አስረድተዋል።

በዞኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 103 ፖፕሮጀክቶች ማለትም በአገልግሎት ፣ በግብርናና በኢንዱስሪዉ ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግ መመዝገባቸውና ከ 8 ሚሊየን ብር እንዳስመዘገቡም አስታዉሰዉ ከ21 ሺህ በላይ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል እንደተፈጠረላቸዉም ተናግረዋል።

መሬት ወስደዉ ያላለሙ ከ62 በላይ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸዉ ተናግረዉ ባለፉት ዘጠኝ ወር ዉስጥ 250 ሄክታር መሬት ማስመለስ መቻሉን እንዱሁም ከ34 በላይ ባለሀብቶች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደተጻፈባቸዉም አብራርተዋል።

በፎረሙ የተገኙ አንዳንድ ባለሀብቶችና ባለ ድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየት መሬት ወስደዉ በሙሉ አቅማቸዉ ወደ ስራ ያልገቡ ባለ ሀብቶች በአፋጣኝ ማልማት እንዳለባቸዉና የማያለሙ ከሆነ መንግስት ተገቢዉን እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባም አመላክተዋል።
የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ ለማስቻል ያሚያጋጥማቸው የቢሮክራሲ፣ የመብራትና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች የሚመለከታቸው አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባናል ብለዋል።

በመጨረሻም በአገልግሎት ዘርፍ ፣ በኢንዱስትሪዉ ዘርፍ፣ በግብርናዉ ዘርፍ ከፍተኛ ሀብት በማፍሰስ ሰፊ ስራ የሰሩና ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠሩ የግሉ ባለሀብቶች የዋንጫና የሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *