በጉራጌ ዞን የዘመናዊ ትምህርት ታሪክ የመጀመሪያ የሆነው የእምድብር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ120 ሚሊዮን ብር ወጪ ተጨማሪ የመማሪ ክፍሎች ግንባታ ለማካሄድ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

በሀገሪቱ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ውጤታማ ለማድረግ ትምህርት ቤቶች ብቁ፣ ተወዳዳሪና ሳይንቲስት የሚሆኑ ምሁራን ለማፍራት በትኩረት መስራት እንደሚጠብቅባቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ር/መስተዳድርና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ ገለጹ፡፡

ይህን የተባለው በውጭ ሀገር የሚኖሩ የቸሃ ወረዳና የእምድብር ከተማ ተወላጆች ከ8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተጨማሪ 5 የመማሪያ ክፍሎች አስገንብተው እየተመረቀ ባለበት ወቅት ነው፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ር/መስተዳድርና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ በፕሮግራሙ ላይ እንዳሉት በሀገሪቱ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ውጤታማ ለማድረግ ትምህርት ቤቶች ብቁ፣ ተወዳዳሪና ሳይንቲስት የሚሆኑ ምሁራን ለማፍራት በትኩረት መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የዞኑ ተወላጆች የትምህርት ግብዓት በማሟላት የትምህርት ቤቶች ደረጃ በማሻሻል የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የሚያደርጉት ሁለንተናው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የመማሪያ መጽሐፍ ለማሳተም የሚያስችል ሀብት ለመሰብሰብ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ህብረተሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ቀጣይ ለሚገነባው ከሙያዊ አገዛ በተጨማሪ 250 ሺህ ብር በክልሉ ትምህርት ቢሮ ስም ለመስጠት ቃል በመግባት።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በፕሮግራሙ ላይ እንደገለጹት የእምድብር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በጉራጌ ዞንና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች ዘመናዊ ትምህርት የተጀመረበት ቢሆንም የትምህርት ቤቱ የተማሪዎቸ መማሪያ ክፍሎች የዕድሜውን ያክል ጥራታቸውን የጠበቁ ያለመሆናቸው ተገንዝበው በውጭ ሀገር የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ጥራቱን የጠበቀ 5 የመማሪያ ክፍሎች ያሉት አንድ ብሎክ በመገንባታቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በዞኑ የትምህርት ቤቶች ደረጃ በማሻሻል የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የትምህርት መሰረተ ልማት የማሟላት ስራዎች ህብረተሰቡ በማሳተፍ ከፍተኛ እርብርብ እየተካሄደ እንደሚገኝ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለጻ የዞኑ ህዝብ የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው ህጻናት በጉራጊኛ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ የማድረግ ስራ ባለፈው አመት በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተጀምሮ በዘንድሮ አመት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ይህም የትምህርት ጥራት ከማሻሻሉም ባለፈ ልጆች ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውንና አከባቢያቸውን ጠንቅቀው እንዲያውቁ እንደሚያስችላቸው አስገንዝበዋል፡፡

አክለውም የአንደኛ ደረጃ የተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍት በማሳተም ተደራሽ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ሁሉም የዞኑ ህዝብ የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ሊያበረክት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የእምድብር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ግንባሩ በርጋ በበኩላቸው የእምድብር አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በሀገሪቱ በርካታ ምሁራን ካፈሩ አንጋፋ ትምህርት ቤቶች ጎራ የሚሰለፍና ወደ ኮሌጅና ዩኒቨርስቲ ደረጃ ማደግ ሲገባው እየፈራረሰ ደረጃው እየወረደ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በት/ቤቱ የተማሩ ተማሪዎችና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የአካባበው ተወላጆች ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር በ120 ሚሊዮን ብር በላይ በሚፈጅ ወጪ ደረጃቸውን የጠበቁ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ር/መስተዳድርና በክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በአቶ አንተነህ ፈቃዱና በጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በአቶ ላጫ ጋሩማ የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስርዓት መከናወኑን ገልጸዋል፡፡

በውጭ ሀገር የሚኖሩ የቸሃ ወረዳና የእምድብር ከተማ ተወላጆች 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነቡት ተጨማሪ 5 የመማሪያ ክፍሎች ያሉት ብሎክ ግንባታ በማጠናቀቅ ዛሬ ተመርቆ ለመማር ማስተማር ስራ ዝግጁ በመሆኑ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የከተማው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት ትምህርት ቤቱ በጥንት በአጼ ኃለስላሴ ዘመነ መንግስት ተቆርቁሮ በርካታ ሙህራን ያፈራና አሁንም እያፈራ የሚገኝ ታሪካዊ ነው።

ትምህርት ቤቱ እድሜ ጠገብ በመሆኑ በእርጅና ምክንያት መጎሳቆል የገጠመው ስለነበር ችግሩን በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ ያሉ የትቤቱ የቀድሞ ተማሪዎችና የአካባቢ ተወላጆች ተረድተው አሁን ላይ የመማሪያ
ክፍሎችና ቁሳቁሶችን ማሟላት በመቻላቸው ደስተኛ መሆናቸውና በቀጣይ ለሚገነባው የበኩላቸውን እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN
ቲዊተር https://twitter.com/home?utm_source=liteAPK&utm_medium=shortcut&first_run=false

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *