ምዕመኑ ትክክለኛ ያልሆኑ አስተሳሰቦችን በማስወገድ በአሉ በአንድነትና በመደጋገፍ ሊያከብር እንደሚገባም ተመላክቷል።
በወልቂጤ ከተማ በደብረሲና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን የስቅለት በአል ሲያከብሩ ካነጋገርናቸው ምእመናን መካከል ወ/ሮ መሪ ነዳና አቶ ፀጋ አሰፋ ይገኙበታል።
ላለፉት ሁለት ወራት በፆም፣ በፀሎትና በስግደት የአብይ ፃም ማሳለፋቸውን በመግለፅ ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቱን እንዲሁም የደረሰበትን መከራና ህመም በማሰብ እኛም ከሱ ፍቅርና ደግነት ለመማር ነው ብለዋል።
ክርስቶስ መልካምነትንና ለወገን መኖርን አስተምሯልና በዚህም እኛም መተሳሰብ ከእሱ ልንማር ይገባል ነው ያሉት።
ሕዝበ ክርስቲያኑ አብሮነቱንና አንድነቱን በማጠናከር እርስ በእርስ በመደጋገፍና በመረዳዳት የስቅለትና ትንሳኤውን በአል ሊያከብር ይገባል ብለዋል።
የወልቂጤ ደብረ ሲና ቅዱስ ገብሬኤል ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ አባ ኤልያስ ታደሰ እንዳሉት እለቱ የሰው ልጆች ከሀጥያትና ከመከራ የዳኑበት ቀን መታሰቢያ መሆኑን ገልፀዋል። በመሆኑም ሰላም ያገኘንበት በአል በመሆኑ እኛም እራሳችን ከክፉ ነገር ለማራቅ መዘጋጀት አለብን ብለዋል።
በዓለ ሰቅለትና ትንሳኤ ክርስቶስ የአዳም ዘርን ነፃ ያወጣበት ክብረ በዓል በመሆኑ ምዕመኑ ትክክለኛ ያልሆኑ አስተሳሰቦችን በማስወገድ በአሉ በአንድነትና በመደጋገፍ ሊያከብር እንደሚገባም አባ ኤልያስ መናገራቸው ወልቂጤ ኤፍኤም ሬድዮ ዘግቦታል።
በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN