ጥር 10/2015 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን የከተራ በዓል ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በድምቀት በሰላም ተከብሯል።
በጉራጌ ዞን በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ ታቦታት ከየአድባራቱና ገዳማቱ ከመንበራቸው ወጥተው በካህናት፣ በዲያቆናት እንዲሁም በምዕመናን ታጅበው በድምቀት ወደ ጥምቀተ ባህር በሰላም ደርሰዋል።
ከበዓሉ በፊት የከተራ በዓል የሚከበርበትን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ገለጻ ከተራ ከበበ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡
የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውሃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተክላል፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ይጥላል፡፡ የምንጮች ውኃ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል፤ ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ ይገደባል፡፡
የከተራ በዓል በየዓመቱ በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ይውላል ። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ የክርስትና እምነት ተከታይ ምእመናን ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴት መሰረት በጥምቀት በዓል ዋዜማ ወንዝ ወይም የምንጭ ውሃ ይገደባል ወይም ይከተራል። ውኃው የሚከተረው በማግስቱ ጥር 11 ቀን የጥምቀት በዓል ስለሚከበር ለሕዝቡ መጠመቂያ እንዲሆን ነው።
ይህ በጥምቀት ዋዜማ የሚደረገው ውሃውን የመከተርና የመገደብ ስርዓትም ” ከተራ ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2015 ዓ.ም የከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲል የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN