በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ አርሶ አሮችና ባለሀብቶች በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ እህል ድጋፍ አደረጉ።

የወረዳዉ ማህበረሰብ ለሀገር መከላከያና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚያደርጉት ድጋፍ በቀጣይም አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል።

የአበሽጌ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ጸጋዬ አምድሳ እንዳሉት የጁንታዉ ኃይል በአገራችን ላይ ወረራ ካካሄደበት ጊዜ ጀምሮ የወረዳዉ ማህበረሰብ የተለያዩ ድጋፎች እያደረገ ይገኛል።

ምልምል የመከላከያ ሰራዊት ከማሳተፍ አንጻር በሁሉቱም ዙር ከዞኑ ከፍተኛ የሆነ ምልምል ሰራዊት ያሳተፉ መሆኑም አስታዉሰዉ ሰራዊቱን ከመደገፍ አንጻር አርሶ አደሩና ባለሀብቱ ካለዉ ላይ እየቀነሰ እየሰጠ እንደሆነም አብራርተዉ በዚህም በመጀመሪያዉ ዙር 17 ሰንጋዎች ፣ በጥሬ ገንዘብ ከ8 መቶ ሺህ ብር በላይ እንዲሁም ከ1መቶ ሺህ ብር በላይ ደረቅ ምግም በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ማስተላለፍ ተችሏል ብለዋል።

በሁለተኛዉ ዙር 6 የእርድ ሰንጋና በገንዘብ ከ9 መቶ 50 ሺህ ብር በላይ ከማህበረሰቡ በማሰባሰብ ለሚመለከተዉ የጸጥታ አካል ያስተላለፉ እንደሆነም አመላክተዉ አሁን ደግሞ በአማራ ክልል በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከራሀብ ለመታደግ አርሶ አደሩ በራሱ ተነሳሽነት ከሚበላዉ ጉርስ ቀንሶ ከ650 ኩንታል በላይ በቆሎ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑም ጠቁመዋል።

የተደረገዉ የእህል ድጋፍ ወደ አማራ ክልል ተጭኖ እየሄደ እንደሆነም ጠቁመዉ የዉጭና የዉስጥ ሀይሎች በአማራና አፋር ክልሎች እያደረሱት ያለዉን መፈናቀል ለማገዝ በቀጣይም አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉም አብራርተዋል።

ከአበሽጌ ወረዳ የዳርጌ ከተማ ነዋሪዉና የድጋፍ አሰባሰብ ኮሚቴ አቶ ሀብታሙ አሳምነዉ እንዳሉት በአካባቢያቸዉ ያሉ አርሶ አደሮችና ባለሀብቶች በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ማንም ሳይጠይቃቸዉ በራሳቸዉ ተነሳሽነት ድጋፍ ማድረጋቸዉም ጠቅሰዋል።

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ላይ ከፍተኛ ንብረት ወድሟል ያሉት አቶ ሀብታሙ ይህም መንግስት ብቻዉን እንደማይወጣዉና የመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።

አቶ አደፍርስ አሰፋና አርሶ አደር አራርሳ ደበሌ በሰጡት አስተያየት የጁንታዉ ሀይል ሀገሪቱ ለማፈራረስ እያደረሰ ያለዉን ጉዳት ለመከላከል በአካባቢያቸዉ በርካታ ወጣቶች ከሀገር መከላከያ በመሆን ጁንታዉን እየተጋፈጡ እንደሆነም አስታዉቀዋል።

መላዉ የወረዳዉ አርሶ አደርና ባለሀብት ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚያደርገዉ ድጋፍ አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉም አብራርተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *