”ሰላም ይስፈን ጥቃት ይቁም” በሚል መሪ ቃል የነጭ ሪቫን ቀን በቸሀ ወረዳ ተከብሯል።
የቸሀ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ምህረት ደንድር እንዳሉት የበአሉ አላማ ሴቶች በሚደርስባቸው ፆታዊ ጥቃት ለማስቆም ፣ አይቶ ላለማለፍ፣ላለመፈፀምና ተፈፅሞ ሲታይ ለሚመለከተዉ አካል አሳልፎ ለመስጠት ቃል የሚገቡበት በአል ነዉ ብለዋል።
በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ዉስጥ ሴቶች በማናቸውም መልክ ያላቸዉ ሚና እጅግ ከፍተኛ ነዉ ያሉት ኃላፊዋ በተዛባ የሥርአተ ፆታ ግንኙነት፣በኋላ ቀር አመለካከት፣ በግንዛቤ እጥረት ምክንያት ለተለያዩ አይነት ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ተጋላጭ ሲሆኑ በሚደርሥባቸዉም ጥቃት ምክንያት ለአካል፣ለጤና ለሥነ ልቦናዊ ችግር እየተዳረጉ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
በዚህ ተግባር ለማህበራዊና ኢኮኖማዊ ችግሮች የሚዳርጉ አልፎም ህይወታቸዉን ያጡ ሴቶች ቁጥር በርካታ እንደሆነ በማመላከት።
በሴቶች ላይ የሚደርሱ ማንኛውም ጥቃቶችን ለመቅረፍ የስርአተ ጾታ እኩልነትን ማስፈንና የህብረተሰቡን አመለካከት ለመቀየር የተጠናከረ የግንዛቤና ንቅናቄ ስራዎችን መሰራት እንዳለበት ገልጸዋል።
በወረዳው በተለያዩ ጊዜያት በሴቶች ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ጾታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ በመሆኑ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እየቀነሱ እንደሆነ አሳውቀዋል።
በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚደርሰው ጾታዊ ጥቃት እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለመቀነስ የሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።
የቸሀ ወረዳ የሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አንድነት ወልዴ እንደገለፁት ህወሀት ሀገር ሲያፈራርስ በሴቶች እና ህጻናት ላይ ጥቃቶችን የፈጸመ በመሆኑ ድርጊቱ የሚወገዝ ነው ብለዋል።
በሴቶችና ህጻናት የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስቀረት ድርጊቱ ከመፈጸሙ በፊት ጥብቅ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል ብለው በወረዳው ይህን ለማድረግ በትምህርት ቤቶች እና በበዓላት ወቅት የግንዛቤ ስራዎችን እንደሚሰሩ ተናግሯል።
በዓሉ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ይህንን ድርጊት ለማስቆም ድርጊቱን በሚፈጽሙ ግለሰቦች ለህግ አሳልፎ መስጠትና አስተማሪ ርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ብለዋል።
አክለውም መሰል ድርጊቶችን እንዳይከሰቱ በተለይ በሴቶች ማህበር በእድርና መሰል ማህበራዊ መሰረቶች ላይ በትኩረት ሊመከርበት ይገባል ሲሉ መግለጻቸው የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
- አካባቢህን ጠብቅ!
- ወደ ግንባር ዝመት!
- መከላከያን ደግፍ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx