በጉራጌ ዞን የታየው የአቮካዶ ምርት ውጤት በሌሎች አካባቢዎችም አስፍቶ መስራት እንደሚያስፈልግ የደቡብ ክልል ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ጥላሁን ከበደ አሳሰቡ።

የአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ በፍራፍሬ ምርቶች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን አርተዳደር አስታወቀ።

በቡታጅራ ማዕከል ሲሰለጥኑ የነበሩት የብልጽግና ፓርቲ የስራ ኃላፊዎች በጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በሞዴል አርሶ አደሮች እየለሙ ያሉ የግብርና ስራዎችን ጎብኝተዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል እንደገለፁት ስልጠናው የሚከታተሉ ሰልጣኞች ከስልጠናው ጎን ለጎን በዞኑ የተሰሩ የልማት ስራዎች በማስጎብኘት ልምድ ይዘው እንዲሄዱ ያስችላቸዋል ብለዋል።

በወረዳው የሚገኙ ሞዴል አርሶ አደሮች የሚገጥማቸው የመልካም አስተዳደርና የዘርፉ ማነቆዎችን በመለየት በቀጣይ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን መፍትሄ ይፈለጋል ነው ያሉት።

አቶ መሀመድ አክለውም አርሶ አደሩ ያለውን ውስን መሬት አሟጦ በመጠቀም በፍራፍሬ ምርቱ የቤተሰቡን የምግብ ፍጆታ እንዲችል ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራበት እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዞኑ መሬት ጾሙን እንዳያድር ታስቦ በተደረገው እንቅስቃሴ በግብርናው ስራ አመርቂ ለውጥ ታይቷል ብለዋል አቶ መሀመድ።

ሀገሪቱ በውጭ ምርት ብቻ ተጠባባቂ እንዳትሆን የበጋ መስኖ ስንዴ ሲሰራ እንደነበር አስታውሰው አሁንም በፍራፍሬው ተግባር 30-40-30 በሚል ዘመቻ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ መሆን መቻሉ አመላክቷል።

የደቡብ ክልል ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ጥላሁን ከበደ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች እየለማ ያለው የአትክልትና ፍራፍሬ ስራ በአጭር ጊዜ ከድህነት ለመውጣት የምናደርገውን ጥረት ያግዛል ብለዋል።

እንደ አቶ ጥላሁን ገለጻ በሞዴል አርሶ አደሮች እየተካሔደ ያለው የግብርና ስራ የውጭ ምንዛሬን ከማስገኘት ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል ፈጥሯል።

በጉራጌ ዞን የታየው የአቮካዶ ፍራፍሬ ምርት በሌሎች አካባቢዎችም አስፍቶ መስራት እንደሚያስፈልግ አቶ ጥላሁን ከበደ አሳስብዋል ።

የደቡብ ክልል የግብርና ቢሮ ሀላፊ አማካሪ አቶ አለም ይርጋ ወ/ስላሴ እንዳሳወቁት በክልሉ 9 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኝ የሚተከል ሲሆን በአንድ ሄክታር እሰከ 2ሺ 500 ችግኞች ይለማል ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ሳሊ መኮነን፣አቶ ጌታሁን ከበደና ዶ/ር ፍቅሬ በጋራ በሰጡት አስተያየት በዘርፉ በመሰማራታቸው ለአካባቢው ማህበረሰብ የምግብ ፍጆታና የወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ችለናል ብለዋል።

ይህ ቢሆንም ግን የገበያ ትስስር ባለመኖሩ፣የጥልቅ ጉድጓድ ውሃ እጥረት ችግርና የኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት ባለማግኘታቸው ለስራው ማነቆ በመሆኑ እንደ መንግስት እነዚህ ችግር እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል።

በመስክ ጉብኝቱ የደቡብ ክልል ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል፣ የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክፍሌ ለማ ጨምሮ ከክልሉ ከተለያየ ዞኖች የመጡ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተውበታል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *