በጉራጌ ዞን የተለያዩ ወረዳና ከተሞች የትምህርት ልማት ሰራዊቱ ለሀገራዊ ጥሪው በተግባር ከእለት ጉርሱ በመቀነስ ሀብት የመሰብሰብ፣የሰብል ማሰባሰብና የዘማች ቤተሰብ ድጋፍ ስራ በወኔ እያከናወነ ይገኛል።

በዛሬ እለት በጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ የሚገኙ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና መምህራን በተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ ድጋፍ አድርገዋል ።

በመስቃን ወረዳ የአካሙጃ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና መምህራን የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ቤተሰቦችን ሰብል የመሰብሰብ ስራን በተለያዩ ቀበሌዎች አከናውነዋል ።

በተለይም በዊጣ ፣ ሸርሸራ ቢዶ ዲራማ እና ጆሌ አንድ ቀበሌዎች የሰብል አሰባሰብ የተከናወነ ሲሆን ከ360 ተማሪዎች እና መምህራን በላይ የተሳተፉ ሲሆን ከዘጠኝ ጥማድ በላይ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል መሰብሰብ ተችሏል ።

በመስቃን ወረዳ የሚገኙ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል የመሰብሰብ ስራ በሌሎች ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና መምህራን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

  • አካባቢህን ጠብቅ!
  • ወደ ግንባር ዝመት !
  • መከላከያን ደግፍ !

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *