በጉራጌ ዞን የብልጽግና ፓርቲ በዞን ማዕከል ለሚገኙ አባላት “መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን ማጽናት ቀጣይ የትግል ምእራፍ” በሚል መሪቃል ስልጠና መሰጠት ተጀመረ።

ሰኔ 26/2015 ዓ/ም

በጉራጌ ዞን የብልጽግና ፓርቲ በዞን ማዕከል ለሚገኙ አባላት “መፍጠንና መፍጠር የወል እውነቶችን ማጽናት ቀጣይ የትግል ምእራፍ” በሚል መሪቃል ስልጠና መሰጠት ተጀመረ።

ስልጠናው በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ለ2 ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ቀጣይነት ያለው ልማትና መልካም አስተዳደር ለማረጋገጥ አሁን ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን መሙላትና የህዝቡ ተሳታፊና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በየደረጃው ያለው የፓርቲው አባላት በትኩረት ሊሰራ ይገባል ተብሏል ።

ገዢው ፓርቲ የአመራሩና የአባላቱን አቅም በማጎልበትና ወጥ የሆነ ግንዛቤ በማስጨበጥ ወቅቱን የሚመጥን ስራ ለመስራት አላማ ያለው ስልጠና ሲሆን የሀገሪቱ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች በማጤን ችግሮችን መፍታት የሚችል የፓለቲካ አመራርና አባል ለመፍጠርና ለመጠን ግብ ተጥሎ እየተሰራ እንደሚገኝ በመድረኩ ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *