በጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽ ጉዳዮች ጽ/ቤት የከተማው ህብረተሰብ የንባብ ባህል ለማጠናከርና ማንባብ እየፈለጉ መጽሐፍትን በቀላሉ ማግኘት የማይችሉ አንባብያን ችግር ለመቅረፍ የመጽሐፍት ውሰት አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ።

ከተለያዩ ግለሰቦችና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ካሰባሰቡዋቸው መጽሐፍቶች በቋሚነት ብዙ የንባብ ደንቦኞችን መፍጠር ተችሏል።

በትምህርት ገበታ ላይ የነበራችሁ ተማሪዎች የእረፍት ጊዜ በመሆኑ ጊዜያችሁን በንባብ ታሳልፉ ዘንድ ጽ/ቤታችን ውስጥ ከ300 በላይ የተለያየ ይዘት ያላቸው የታሪክ፣ የፍልስፍና የሳይኮሎጂና ልብ ወለድ መፅሃፍቶች ስላሉን በውሰት ወስዳችሁ ማንበብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

አድራሻ፦ ከዋርካው ጀርባ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግቢ ያለ ቢሮ ውስጥ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ያገኙናል።

ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!!

የቡኢ ከተማ አስተዳድር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *