መስከረም 15/2015 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን የቡታጅራ ከተማ እና አካባቢ ልጆች ህብረት አነስተኛ ገቢ ላላቸውና አቅመ ደካማ ለሆኑ 200 ቤተሰብ ማዕድ አጋራ።
የመስቀል በዓልን በማስመልከት የተካሄደው የማዕድ ማጋራት ዘንድሮ ሲካሄድ የአሁኑ ለ5ኛ ጊዜ መሆኑንም ተገልጿል።
የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን እያከናወነ የሚገኘው የቡታጅራ ከተማ እና አካባቢ ልጆች ህብረት በየዓመቱ ለመስቀል እና ለኢድ አል-አድሃ አረፋ በዓላት ላለፉት አራት አመታት በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ተለይተው ለሚቀርቡ 200 ቤተሰቦች 10 ሰንጋዎችን አዘጋጅቶ ማዕድ እንደሚያጋራ የአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ገልጿል።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ነጋሽ መሀመድ ህብረቱ ማዕድ ማጋራትን ጨምሮ የተለያዩ ማህበራዊ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በተለይም የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ተቀራርቦ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ጥረት እያደረገ እንደሆነ ጠቅሰው ህብረቱ በቡታጅራ መሰናዶ ትምህርት ቤት የአራት መማሪያ ክፍሎች ግንባታ ማስጀመሩን ጠቁመዋል።
ኑራቸውን በአንጎላ ያደረጉት የቡታጅራ ከተማ እና አካባቢ ልጆች ህብረት አባል አቶ አሸናፊ ተስፋዬ በበኩላቸው የህብረቱን ማህበራዊ አገልግሎት ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ተሳታፊዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመሆኑ በቋሚነት ማህበራዊ ድጋፍ ማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ተናግረዋል።
በጉራጌ ዞን በድምቀት በሚከበረው የመስቀል በዓል የእንስሳት እርድ የሚከናወነው መስከረም 15 ነው።(ኢዜአ)
ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ