በጉራጌ ዞን የበጎ ፈቃድ ቀን ምክንያት በማድረግ በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል ተኝቶ ለሚታከሙ የአዕምሮ ህሙማን የአልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን ተገለጸ፡፡

ጳጉሜ1/2014 ዓ.ም

በጉራጌ ዞን የበጎ ፈቃድ ቀን ምክንያት በማድረግ በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል ተኝቶ ለሚታከሙ የአዕምሮ ህሙማን የአልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን ተገለጸ፡፡

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ መቀጠሉን የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ፡፡
የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዶ ድንቁ እንደገለጹት በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አረጋዊያንና አቅመ ደካሞችን መርዳት፣ የአረንጓዴ ልማት የችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳ፣ የክረምት የተማሪዎች ማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት፣ የዘማች ቤተሰብ የመደገፍና በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

በሀገሪቱ የተከበረውን የበጎ ፈቃድ ቀን ታሳቢ በማድረግ ሆስፒታሉ ተኝቶ ለሚታከሙ የአዕምሮ ህሙማንና የሱስ ማገገሚያ ታካሚ ወጣቶች የአልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች የጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይና ወጣቶችና ስፖርት መምሪያዎች ከዞኑ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ቀጣይ በሚከበሩ አዲስ አመትና የመስቀል በዓል አረጋዊያንና አቅመ ደካሞች እንዲሁም የዘማች ቤተሰቦች የመደገፍና አብሮ የማሳለፍ በጎ ተግባር ህብረተሰቡ አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል ጠቅላላ ሀኪም ደ/ር አረጋኸኝ ታደሰ በበኩላቸው በሆስፒታሉ ተኝቶ የሚታከሙ የአይምሮ ህሙማን የሚሰጠው ህክምና በስፋት መቀጠሉንና የህሙማን ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል የአይምሮ ህሙማን ተኝቶ መታከሚያና ማገገሚያ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ከጀመረ አጭር ጊዚ ቢሆን ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን ህክምና አበረታች መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ የህክምና ክፍሉ በሰውና በቁሳቁስ በማደራጀት የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስፋት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ዛሬ በሀገር ደረጃ የተወሰነው የበጎ ፈቃድ ቀን ታሳቢ በማድረግ በሆስፒታሉ ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን ለተደረገላቸው ድጋፍ በሆስፒታሉ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ድጋፍ ከተደረገላቸው ታማሚዎች መካከል ወጣት ምንተስኖት አዳሙና አንዱዓምላክ አሰፋ በሰጡት አስተያየት በሆስፒታሉ ጥሩ ህክምናና እንክብካቤ እንደሚደረግላቸው ገልጸው ዛሬ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ፡፡

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *