በጉራጌ ዞን የህግና አስተዳደር ዘርፍ ተቋማት የመንግስት ሰራተኞች በጋራ በመሆን የተለያዩ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችን አጠናክረው እየሰሩ እንደሚገኙ የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታወቁ።


ሰራተኞቹ ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ደም ለሚሹ ወገኖች ደማቸውን ለግሰዋል።
የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ አካሉ እንደገለፁት የህግና አስተዳደር ዘርፍ ተቋማት ስር የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ከደመወዛቸው 32 ሺህ ብር በማሰባሰብ የአረጋውያን ቤት ለመጠገን በዝግጅት ላይ መሆናቸው ገልፀዋል።
200 ችግኞች በህዳሴ ፍሬ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መትከላቸውና ለ59 ታራሚዎች የምገባና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጋቸውን የተናገሩት የአስተዳደሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ አካሉ አንድም ሰው በደም እጦት ምክንያት መሞት የለበትም በሚል እሳቤ ሰራተኞቹን በማስተባበር 25 ዩኒት ደም መለገሳቸው አስታውቀዋል።
የህብረተሰቡ በተለይም የመንግስት ሰራተኛው የማንብ ባህል በማዳበር በሀገር ልማት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማስቻል 200 ሺህ ብር ግምት ያላቸው 800 የተለያዩ መፅሐፍት ከተለያዩ በጎ አድራጊ አካላት በማሰባሰብና የንባብ ካፌ ቤት አስመርቆ በመክፈት አገልግሎት እንዲሰጥ ማስቻሉን ተናግረዋል።
የህግና አስተዳደር ዘርፍ ተቋማት የመንግስት ሰራተኞች አጠቃላይ በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መንግስት ሊያወጣው የነበረው 500 ሺህ ብር ማዳን መቻላቸውን ተናግረዋል።
የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ሰራተኛ ወ/ሮ መችበዙ ገብሬ ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ደም ለሚሹ ወገኖች ደማቸውን ሲለግሱ አግኝተን በሰጡን አስተያየት በጦር ግንባር ሆኖ ለሚዋደቁና ሌሎች ደም ለሚሹ እናቶች ፣ሴቶችና ድንገተኛ አደጋ ለሚደርስባቸው ወገኖችን ለመታደግ ደም ለመስጠት እንዳነሳሳቸው ተናግረዋል።
ወ/ሮ መችበዙ ገብሬ አክለውም በጉራጌ ዞን የህግና አስተዳደር ዘርፍ ተቋማት ስር የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ከወር ደመወዛቸው 3 በመቶ በማዋጣት የ2 የአረጋውያን ቤት ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑንና በወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ተገኝተው የምገባና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጋቸውገልፀው ። አጠቃላይ የሚሰሩት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።
በህግና አስተዳደር ዘርፍ ተቋማት የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሰራተኛ አቶ ሰፊ ቅባቱ በበኩላቸው ከተለያዩ 7 ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በመሆን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙ በተለይም በክረምቱ ወቅት ደም በመለገስ፣ ችግኝ በመትከል፣ የአረጋውያን ቤት በመጠገን፣ አልባሳት በማሰባሰብና በሌሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች መሳተፋቸውን ተናግረዋል።
ሰራተኞቹ ይህ የሚያደርጉት ተሳትፎ በቀጣይ አጠናክረው አደንደሚቀጥሉ መግለፃቸው የዘገበው የጉራጌ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *