በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የተጀመረው ሳምንታዊ የቅዳሜ ገበያ ሰውሰራሽ የመሰረታዊ ፍጆታ እና የግብርና ምርቶች አቅርቦት እጥረት ችግር ለመቅረፍ እንደሚያግዝ አንዳድ ሸማቾች ተናገሩ ።

ህገወጥ የንግድ ስርዓት ለመከላከል ህብረተሰቡ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን መስራት እንደሚጠበቅ የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

በምርት እድገትና በኢኮኖሚ የላቀ ደረጃ ላይ ለመድረስ ቀልጣፋና ዘመናዊ እንዲሁም ሁሉንም በየደረጃው ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል የግብይት ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ።

ይህን የግብይት ስርዓት ምርትን በተፈለገው መልኩ ወደ ገበያ ለማቅረብና ሸማቹ ህብረተሰቡም የሚፈልገውን ምርት እና አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ አግኝቶ ኑሮውን በአግባቡ እንዲመራ ያስችለዋል ።

ለዚህም ነው የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በወልቂጤ ከተማ ሳምንታዊ የቅዳሜ ገበያ በማቋቋም ወደ ስራ የገባው።

አንዳንድ ያነጋገርናቸው ሸማቾች በከተማው ሳምንታዊ ገበያ ባለመኖሩ የፋብሪካና የግብርና ምርቶች በሚፈልጉት ጥራት እና መጠን ለማግኘት ሲቸገሩ እንደነበር ተናግረዋል።

እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ ገለፃ በወልቂጤ ከተማ የተጀመረው ሳምንታዊ የቅዳሜ ገበያ ሰውሰራሽ የመሰረታዊ ፍጆታ እና የግብርና ምርቶች አቅርቦት እጥረት ችግር በዘላቂነት በመቅረፍ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ያደርጋል።

በከተማው የተጀመረው ሳምንታዊ የቅዳሜ ገበያ በመጀመሪያ የግብይት ወቅት በቂ የምርት አቅርቦት እንዳልነበረ የተናገሩት ሸማቾቹ በቀጣይ ክፍተቶችን ለመሙላት መንግስት አስፈላጊ የሆኑ ምርቶች በሚፈለገው መጠንና ጥራት በማቅረብ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መሀመድ አማን እንደተናገሩት እንደ ሀገር የተከሰተው የዋጋ ንረት ለመከላከል ከህብረት ስራ ጽህፈት ቤት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ነው።
እንደ ኃላፊው ገለጻ አርሶ አደሮች የሚያመርቱት ምርት በቀጥታ ከማሳ ወደ ገበያ በማቅረብ የሸማቾች ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው።

በወልቂጤ ከተማ የተጀመረው ሳምንታዊ የቅዳሜ ገበያ ማህበረሰቡ የሚፈልጋቸው የፋብሪካና የግብርና ምርቶች በቀላሉ እንዲያገኝ ከማስቻል ባለፈ ሀገሪቱ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የምታስገባቸው ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ያስችላል ብለዋል።

አርሶ አደሮች የሚያመርቷቸው ምርቶች ሳይባከንባቸው እና ደላሎች ጣልቃ ሳይገቡባቸው በሚፈልጉት ስዓትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ እንዲያቀርቡ እድል እንደሚፈጥርላቸው አስገንዝበዋል።

በዞኑ በህገወጥ የንግድ ስራ በተሰማሩና እና ሰው ሰራሽ የምርት እጥረት እንዲከሰት በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ህብረተሰቡ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን መስራት እንደሚጠበቅበት ኃላፊው አሳስበዋል።

የጉራጌ ዞን ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ነጋሽ በበኩላቸው ሸማቹ ማህበረሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ የህብረት ስራ ማህበራትና ዩኒየኖች ምርቶቻቸው ወደ ገበያ በማቅረብ ለሸማቾች እንዲያቀርቡ እየተስራ ነው ብለዋል።

በዞኑ ማዕከል ወልቂጤ ከተማ የተቋቋመው ሳምንታዊ ቅዳሜ ገበያ ጅማሬው ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮች በማረም ሁሉም የምርት አይነቶች እንዲቀርቡ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

አያይዘውም አቶ ጌታሁን ገበያው በየወረዳው የሚገኙ ማህበራት ምርቶቻቸው በቀጥታ ለሸማቾች ለማቅረብ እድል ይፈጥርላቸዋል። በዚህም ለማህበራት የገበያ ትስስር ከመፍጠር ባለፈ ገበያን ለማረጋጋት ያስችላል ብለዋል

በየወረዳው የሚገኙ ማህበራት ምርቶቻቸው ወደ ገበያ በሚያቀርብበት ወቅት ሸማቾች ተረጋግተው የሚፈልጓቸው ምርቶች መሸመት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

አያይዘውም አቶ ጌታሁን በዘርፉ የሚፈለገው ውጤት ለማምጣት ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታፈሰ ዳምጠው በሰጡት አስተያየት በገበያ ላይ የሚስተዋለው ሰውሰራሽ የምርት እጥረት ለዋጋ ንረት ምክንያት በመሆኑ ሸማቹ ማህበረሰብ ደላሎች ጣልቃ ሳይገቡ በነጻነት እንዲገበያዩ መንግስት በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

የገበያው መቋቋም ሰውሰራሽ የምርት እጥረት ለመከላከልና ቋሚ ሳምንታዊ ገበያ ለማቋቋም ያለመ ተግባር በመሆኑ ህብረተሰቡ የሚፈልገው ምርት በገበያው እንዲያገኝ ያስችለዋል ብለዋል ሲል የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *