በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የአይን ህክምና አገልግሎት መስጫ ማዕከል ማስፋፊያ ግንባታ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ማዕከሉ በወልቂጤ ከተማ ጤና ጣቢያ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን አገልግሎት የሚሰጡ አምስት ክፍሎች አሉት።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበራ ወንድሙ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ወቅት እንደገለጹት ኦርቢስ አለም አቀፍ በዞኑ ውስጥ በ 20 አመታት ውስጥ በርካታ የአይን ጤና ህክምና አገልግሎቶችን ሲሰጥ መቆየቱን ገልጸዋል ።

የአይን ህክምና አገልግሎት ለማስፋፋት በሚደረገው ጥረት ዞኑ በትኩረት እንደሚሰራ የገለጹት አቶ አበራ ወንድሙ ሁሉም ማህበረሰብ በየአካባቢው ህክምና እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን በበኩላቸው በመንግስት ያልተሸፈኑ የጤና አገልግሎቶች ክፍተት በመሙላት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የአጋር ድርጀቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል ።

በትራኮማ፣ የአይን ሽፋሽፍት ወደ ውስጥ በመቀልበስና በሌሎች ምክንያቶች የሚከሰተውን አይነ ስውርነት ለመከላከል ከመንግስት ጋር በመሆን በተደረገው ሰፊ ርብርብ ብዙ ሺህ ወገኖች መታደግ መቻሉን ተናግረዋል ።

የኦርቢስ አለም አቀፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ዶሪስ ማቻትያ የወልቂጤ ከተማ 2 ተኛ ደረጃ የአይን ህክምና ማዕከል የማስፋፊያ ግንባታ መጥው በማየታቸው መደሰታቸውንና ኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለው ጉብኝት ለረጅም ጊዜ የታቀደ ነው ብለዋል።

የአይን ህክምና አገልግሎቱን ከዚህ የተሻለ ለማድረግ እንደሚጥሩ የተናገሩት ዶክተር ዶሪስ የኦርቢስ ተግባራት ቀደም ባሉት ዓመታት ጀምሮ እዚህ የደረሰው ከዞኑ አስተዳደር ጀምሮ ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ትልቅ ስራ ሰርተዋል ብለዋል ።

በእለቱም ለኦርቢስ አለም አቀፍ የስራ ኃላፊዎች የእውቅና ሰረተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

የወልቂጤ ከተማ ጤና ጣቢያ እና በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ሆሌ ጤና ኬላ የአይን ህክምና ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ የዞኑና የከተማው የስራ ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ጉብኝት አድርገዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *