በጉራጌ ዞን ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ የፈተና መስጫ ማዕከላት መስጠት ተጀመረ።

ሰኔ 26/2015
በጉራጌ ዞን ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ የፈተና መስጫ ማዕከላት መስጠት ተጀመረ።

በ2015 ዓ.ም በሚሰጠው ክልል አቀፍ ፈተና 32 ሺህ 132 ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ ከዞኑ ትምህርት መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የዘንድሮ የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከወትሮ በተለየ ከኩረጃ የጸዳ ፈተና ለመስጠት የተሰራ ሲሆን ተማሪዎች ከተማሩበት ትምህርት ቤት ውጭ በ206 የፈተና መስጫ ክላስተሮች እየተፈተኑ ይገኛሉ።

ይህ ደግሞ ተማሪዎች በራሳቸው ጥረት ሳይኮራረጁ እንዲፈተኑ አስችሏቸዋል።

በመሆኑም ጎበዝ ተማሪዎች ሳይረበሹ በመፈተናቸው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እድል ይፈጥርላቸዋል።
ተማሪዎቹ በዛሬው እለት አራት የትምህርት አይነቶች የሚፈትኑ ሲሆን በነገው እለትም ይቀጥላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *