በጉራጌ ዞን ከ80 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 17 የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ፕሮጀክቶች ለትራፊክ ክፍት ሆኑ።

የመንገዶቹ መገንባት የእለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ከማጠናከር በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያሳድግላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።

በደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አበባየሁ ታደሰ እንደገለፁት ህብረተሰቡ የሚጠይቃቸው የመንገድ መሰረተ ልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ መንግስት እየሰራ ይገኛል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ በክልሉ ባለፉት አስርት አመታት 4ሺህ 2መቶ ኪሎሜትር ሁሉአቀፍ የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ተገንብተው አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል።

በቀጣይ በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሁሉአቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጨምር ኃይሌ በበኩላቸው በ2014 በጀት አመት 64 የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ በማጠናቀቅ ለትራፊክ ክፍት ሆነዋል ብለዋል።

እስካሁን በተከናወኑ የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን የገለፁት አቶ ጨምር ይህን መሰል ተግባር ለማጠናከር መንግስት ህብረተሰቡን በማሳተፍ ቀጣይነት ያለው ተግባር ያከናውናል ብለዋል።

በበጀት አመቱ በመንግሥት በተበጀተው 350 ሚሊዮን እና በህብረተሰብ ተሳትፎ 457 የመንገድ ጥናትና ዲዛይን፣ 46 የድልድይ ጥናትና ዲዛይን፣ 765 ዲችና ካምፐር፣ 641 የጠጠር መንገድ ስራ ማጠናቀቅ፣ 403 ማይነር ስትራክቸሮች ግንባታ ማጠናቀቅ እንዲሁም የ26 ድልድዮች ግንባታ ማጠናቀቅ ተችሏል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክፍሌ ለማ መንግስትና ህዝብ ተባብረው ከሰሩ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጡ ተግባራት ማከናወን እንደሚቻል ገልጸዋል።

መንግስት የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ የመመለስ አቅሙን እንዲዳብር ሁሉም ተቀናጅቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

እንደ አቶ ክፍሌ ገለጻ የሀገሪቱ ሰላም፣ የህዝቡ የአንድነት፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት እሴቶች እንዲጎለብቱ ህዝቡ መስራት ይጠበቅበታል ።

የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ እንደገለጹት በ2014 በጀት አመት በጉራጌ ዞን ደረጃ ከታቀዱ 26 የሁሉአቀፍ ተደራሽ የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ የ17 ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናቋል ብለዋል።

ለእነዚህ ፕሮጀክቶች ግንባታ 80 ሚሊዮን 574ሺ 749 ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን 111 ነጠብ 9 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲሆን ተጨማሪ 4 ድልድዮች፣ 82 አነስተኛ ስትራክቸሮችን ተገንብተው ለትራፊክ ክፍት እንደሆኑ አስረድተዋል።

እነዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ 32 ቀበሌዎች የሚያገናኙ መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

ለትራፊክ ክፍት የሆኑ መንገዶች ዘላቂ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥበቃና እንክብካቤ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

ያነጋገርናቸው ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት ከዚህ ቀደም በነበረባቸው የመንገድ እጥረት ለከፍተኛ እንግልት ይዳረጉ ነበር።

አሁን የመንገዱ መገንባት የግብርና ግብዓት በቀላሉ ለማስገባት፣ ወደ ጤና ተቋማት ለመሄድና ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ለመሸኘት ይገጥማቸው የነበረውን ጫና ቀንሶላቸዋል።

በመሆኑም መንገዱ ዘላቂ አገልግሎት መስጠት እንዲችል በባለቤትነት እንደሚጠብቁ ገልጸው በቀጣይ የመብራትና ሌሎች የመሰረት ልማት እንዲሰራላቸው መንግስትን ጠይቀዋል።

በመጨረሻም በመንገድ ስራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ማህበራት፣ የስራ ኃላፊዎች፣ ተቋራጮች የእውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *