በዘማች ቤተሰቦች የሰብል ማሰባሰብ ዘመቻ ምክንያት ለአንድ ሳምንት ተቋርጦ የነበረው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት መጪው ሰኞ ጀምሮ የመማር ማስተማሩ ስራ እንደሚጀመር ተገልጿልም።
የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ እንደገለጹት በመላው ሀገሪቱ በተቀናጀ ሁኔታ ህዝቡ አንድ በመሆን መከላከያ ሰራዊቱን በመደገፍ አጋርነቱን እያሳየ ይገኛል። በጉራጌ ዞንም የዚሁ ድጋፍ አካል በመሆን የትምህርት ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
በሀገራችን በሰሜኑ ክፍል እየተካሄደ ባለው የህልዉና ጦርነት በግንባር ተገኝተዉ እየተዋደቁ ለሚገኙ ወገኖቻች አጋርነታቸው ለመግለፅ እና ድጋፍ እንዲሆናቸው በማሰብ ሰብል የመሰብሰብ ፣ ሀብት የማሰባሰብ፣ ደም የመለገስ እና ከተሞች የማፅዳት ስራ ላይ በመሰማራት በዞኑ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ የትምህርት ተቋማት ለአንድ ሳምንት ትምህርት በማቋረጥ በስፋት ሲሰሩ ቆይተዋል።
በ21 ወረዳዎችና በ5 ከተማ መስተዳደሮች በሚገኙ ሁሉም የትምህርት ተቋማት ሀብት የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ እንደነበረም ተናግረዉ በዚህም ከተማሪዎች ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ፣ ከትምህርት ተቋማት የውስጥ ገቢ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ እንዲሁም መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ከሚያገኙት ደመወዝ እስከ 20% በመወሰን በአጠቃላይ ከ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታዉቀዋል።
ከዚህም በተማሪዎችና መምህራኖች ቅንጅታዊ ስራ በቆሎ 96 ሄክታር ፣ ጤፍ 19 ሄክታር፣ ስንዴ 6 ሄክታር ፣ ገብስ 2 ሄክታር እንዲሁም ማሽላ 5 ሄክታር መሬት በድምሩ 128 ሄክታር መሬት ሰብል የመሰብሰብ ስራ ለዘማች ቤተሰቦች እና አቅመ ደካማ ለሆኑ ሰዎች መሰራቱም አብራርተዋል።
በመምህራኖች፣ በተማሪዎችና በሌሎችም ቀና ትብብር ደም የማሰባሰብ ስራዉ በትኩረት እየተሰራ እንደነበርና 475 ዩኒት ደም ማሰባሰብ መቻሉን ተናግረዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል በጉራጌ ዞን በሁለም አካባቢዎች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት በመዝጋት ተማሪዎችና መምህራን አንድ ላይ በመሆን የዘማች ቤተሰብ ሰብል የማሰባሰብ ፣ ደም የመለገስ፣ ከተሞች የማፅዳት እና ሀብት የማሰባሰብ አላማ እንዲሳካ ለተሳተፉ ተማሪዎች ፣ መምህራኖችና እንዲሁም ሲያስባብሩ ለነበሩ አካላት ልባዊ ምስጋና አቅርበው።
በመጨረሻም ተቋርጦ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የፊታችን ሰኞ በቀን 04/04/2014 ዓ.ም የሚቀጥል በመሆኑ ተማሪዎች እና መምህራኖች የማካካሻ ፕሮግራሞች በማዘጋጀት የትምህርት ክፍለ ጊዜያቸውን መጠቀም እንዳለባቸው ገልፀዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።
- አካባቢህን ጠብቅ!
- ወደ ግንባር ዝመት!
- መከላከያን ደግፍ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx