በጉራጌ ዞን ከአደረጃጀት ጥያቄ በተያያዘ የዞኑ የጸጥታ ሁኔታ ያለበት ደረጃ እና በቀጣይ አቅጣጫ ዙሪያ በወልቂጤ ከተማ ውይይት ተካሄደ።

ነሐሴ22/2014 ዓ.ም

በጉራጌ ዞን ከአደረጃጀት ጥያቄ በተያያዘ የዞኑ የጸጥታ ሁኔታ ያለበት ደረጃ እና በቀጣይ አቅጣጫ ዙሪያ በወልቂጤ ከተማ ውይይት ተካሄደ።

የውይይት መድረኩን አስመልክተው መግለጫ የሰጡት የጉራጌ ዞን ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ ህዝቡ የጠየቀውን የአደረጃጀት ጥያቄ ምላሽ አልተሰጠም በሚል ስራ አቁሞ ቤት የመቀመጥ አድማው የጸጥታ መዋቅሩ ማስቆም ያለመቻሉ ከክልል ጀምሮ በክፍተት መገምገሙን ተናግረዋል።

የአደረጃጀት ጥያቄ በተመለከተ ህዝቡ በህጋዊ መንገድ ከመጠየቅ ውጪ ህብረተሰቡ ከስራ ውጪ ሊያደርጉና የጸጥታ ስጋት ለመፍጠር የአድማ እንቅስቃሴ ለማድረግ በሚሞክሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል።

የጉራጌ ዞን የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊና የሰላምና ጸጥታ መምሪያ ተወካይ አቶ አብድልሃፊዝ ሁሴን እንደገለጹት የጸጥታ መዋቅር ከየትኛውም የፖለቲካ ተሳትፎ ገለልተኛ በመሆን የህብረተሰቡን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚያውኩ የጸጥታ ችግሮች የመቅረፍ ግዴታ አለበት።

ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር የአካባቢውን ሰላም የሚያውኩ አካላት በመምከር አደብ የማስገዛቱ ስራ ከመስራት ጎን ለጎን ለጸጥታ ስጋት የሚሆን አካል ሲያጋጥም በህግ ተጠያቂ የማድረግ ስራ መሰራት እንዳለበት ኃላፊው ተናግረዋል።

በውይይት መድረኩ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ ከወረዳዎችንና ከከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የጸጥታ አመራሮች ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *