በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ መንጠርና አምበሊ ቀበሌዎች በእሳት አደጋ ቤት ንብታቸው የወደመባቸው ዜጎች የዞኑና የወረዳው ከፍተኛ አመራሮች ያሉበት ሁኔታ ጎበኙ ።

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች በ26 ቤቶች ላይ በደረሰው እሳት አደጋ 30 ሚሊየን 818 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ በወረዳው ግብርና ልማት ፅ/ቤት የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት አስተባባሪ አቶ እንዳልካቸው ደሳለኝ ገልፀዋል ።

የጉራጌ ዞን ቀይ መስቀል ማህበርና የዞኑ አደጋና መከላከልና ዝግጅት የመመገቢያና የአልባሳት ቁሳቁሶች ለተጎጂ ቤተሰቦች ድጋፍ አድርገዋል ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪአቶ መሀመድ ጀማልና የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ ጨምሮ የዞኑና የወረዳው አስተባባሪና አመራሮች ለተጎጂ ቤተሰቦች ጠይቀዋል ።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ እንደገለፁት የእሳት አደጋው መከሰቱን እጅግ የሚያሳዝን እንደሆነ ገልፀው በዚህ አደጋ ቤት ንብረት የወደመባቸው ወገኖች የዞኑንም ይሁን የወረዳው መንግስት በተቻለው አቅም ከጎናቸው ነው ብለዋል ።

ለጊዜው ለተጎጂው ቤተሰቦች የዞኑ ቀይ መስቀልና አደጋ መከላከልና ዝግጁነት በማስተባበር የመመገቢያና የአልባሳት ቁሳቁስ ለተጎጂ ቤተሰቦች ድጋፍ መደረጉን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው በቀጣይም የድጋፍ አሰባሰብ ኮሚቴ በማዋቀር የግንባታ እቃዎችና ሌሎችም ድጋፍች በተቻለው አቅም ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯልም ብለዋል ።

በዚህ የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳቱ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ወጣቱ፣ባለሀብቱና መላው ማህበረሰብ ከጎናቸው እንዲቆምም ጠይቀዋል ።

በእዣ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት አስተባባሪ አቶ እንዳልካቸው ደሳለኝ በወረዳው መጋቢት 7 እና 8/2014 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት በመንጠር እና አንበሊ ቀበሌዎች ሁለት የእሳት አደጋዎች የተከሰቱ ሲሆን በድምሩ 26 ቤቶችና 30 ሚሊየን 818 ሺህ ብር መውደሙንም ገልፀዋል ።

እነዚህ የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የገለፁት አቶ እንዳልክ ከዞኑ ቀይ መስቀልና ከዞኑ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ለጊዜያዊ መጠቀሚያ የሚሆኑ የአልባሳትና የመመገቢያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል ።

በቀጣይም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እነዚህ ተጎጂዎች የመጠየቅና ድጋፍ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት አቶ እንዳልክ ህብረተሰቡም ወቅቱ ደረቃማና ነፋሻማ በመሆኑ እንደዚህ አይነት የእሳት አደጋ ነቅቶ ሊጠብቅ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል የዘገበው የወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *